ዘፍጥረት 7:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዝናቡም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዘነበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ ዘነበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝናብም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዘነበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዝናቡም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰማይም መስኮቶች ተከፈቱ ዝናቡም አርባ ቀንም አርባ ሌሊት በምድት ላይ ሆነ። |
ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፥ ውሃውንም ጠጣ፤ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኃይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ።
“እኔም፥ ከዚህ ቀደም እንዳደረኩት፥ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በተራራው ላይ ተቀመጥሁ፥ በዚህም ጊዜ ጌታ ደግሞ ሰማኝ፤ ጌታ ሊያጠፋህ አልወደደም።
ከዚህም በኋላ እንደገና አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እህል ሳልቀምስና ውኃ ሳልጠጣ በጌታ ፊት በግንባሬ ተደፍቼ ቆየሁ። ይህንንም ያደረግኹት ስለ ሠራችሁት ኃጢአት ሁሉ፥ እርሱንም ለማስቆጣት በጌታ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጋችሁ ነበር።
የድንጋዩን ጽላቶች፥ ጌታ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን የፈጸመባቸውን ጽላቶች፥ ለመቀበል ወደ ተራራ በወጣሁ ጊዜ፥ በተራራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀምጬ ነበር፤ እህል አልቀመስኩም፥ ውኃም አልጠጣሁም።