Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 19:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፥ ውሃውንም ጠጣ፤ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኃይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስለዚህም ተነሥቶ በላ፤ ጠጣም፤ በምግቡም ብርታት አግኝቶ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ኮሬብ እስኪደርስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተጓዘ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፥ ውሃውንም ጠጣ፤ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኀይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ተነ​ሥ​ቶም በላ፤ ጠጣም፤ በዚ​ያም በበ​ላው የም​ግብ ኀይል እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ተነሥቶም በላ፤ ጠጣም፤ በዚያም ምግብ ኀይል እስከ እግዚአብሔር ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 19:8
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጌታ ጋር ነበረ፤ ምግብ አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም። በጽላቶቹም ዓሥሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።


አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ።


ከዚህም በኋላ እንደገና አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እህል ሳልቀምስና ውኃ ሳልጠጣ በጌታ ፊት በግንባሬ ተደፍቼ ቆየሁ። ይህንንም ያደረግኹት ስለ ሠራችሁት ኃጢአት ሁሉ፥ እርሱንም ለማስቆጣት በጌታ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጋችሁ ነበር።


ሙሴም ወደ ደመናው ውስጥ ገባ ወደ ተራራውም ወጣ፤ ሙሴም በተራራው ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቆየ።


ሙሴም የምድያን ካህን የሆነውን የአማቹን የይትሮን በጎች ያሰማራ ነበር፤ በጎቹን ከምድረ በዳው ማዶ ነዳቸው፥ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ ኮሬብ መጣ።


እርሱ ግን፥ “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ በድካም ፍጹም ይሆናል” አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል እንዲያድርብኝ በበለጠ ደስታ በድካሜ መመካትን እወዳለሁ።


ለአርባ ቀን በዲያብሎስ ተፈተነ። በእነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፤ ቀኖቹም በተፈጸሙ ጊዜ ተራበ።


በሰይጣንም እየተፈተነ አርባ ቀን በበረሓ ቆየ። ከአራዊትም ጋር ነበር፤ መላእክትም አገለገሉት።


ጌታ በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ ይጤስ ነበር፤ ጢሱም ከእቶን እንደሚወጣ ጢስ ይወጣ ነበር፥ ተራራውም ሁሉ እጅግ ተናወጠ።


ጌታም አሮንን፦ “ሙሴን ለመገናኘት ወደ ምድረ በዳ ሂድ” አለው፤ ሄዶም በእግዚአብሔር ተራራ ተገናኘው፥ ሳመውም።


የጌታም መልአክ ተመልሶ መጥቶ “የምትሄድበት መንገድ ሩቅ ስለ ሆነ፥ ተነሥተህ ብላ!” ሲል ዳግመኛ ኤልያስን ቀሰቀሰው።


ከወንዙም ውሃ ጠጣ፤ ቁራዎችም ዘወትር ጧትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች