ዘፍጥረት 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርም ሴቲቱን፦ “ይህ ያደረግሽው ምንድነው?” አላት። ሴቲቱም፥ “እባብ አሳተኝና በላሁ” አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላክ ሴቲቱን፣ “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” አላት። እርሷም፣ “እባብ አሳሳተኝና በላሁ” አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን “ይህ ያደረግሽው ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቃት። እርስዋም “እባብ አታለለኝና በላሁ” አለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፥ “ይህን ለምን አደረግሽ?” አላት። ሴቲቱም አለች፥ “እባብ አሳተኝና በላሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፦ ይህ ያደረግሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም አለች፦ እባብ አሳተኝና በላሁ። |
ዮሴፍም፥ “ለምን እንዲህ ያለ ነገር አደረጋችሁ? እንደ እኔ ያለ ሰው ስውር ነገርን የሚያውቅበት ልዩ ጥበብ እንዳለው አታውቁምን?” ሲል ጠየቃቸው።
ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከጌታ የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ነገር ግን ዋሽቶ ነበር።
ነገር ግን ሴት ልጅ ብትወልድ እንደ ወር አበባዋ ጊዜያት ሁለት ሳምንት ያኽል የረከሰች ትሆናለች፤ ከደምዋም እስክትነጻ ድረስ ስልሳ ስድስት ቀን ትቀመጥ።
ሳሙኤል ግን “ያደረግኸው ነገር ምንድነው?” ሲል ጠየቀው። ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ ሠራዊቱ መበታተኑን፥ አንተም በቀጠርኸው ጊዜ አለመምጣትህን፥ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ መሰብሰባቸውን አየሁ፤
ሳኦልም፥ “ሠራዊቱ ከአማሌቃውያን ማርከው ያመጧቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጦቹ በጎችና በሬዎች ለጌታ ለአምላክህ መሥዋዕት እንዲሆኑ ሳይገድሉ የተዉአቸው ናቸው፤ የቀሩትን ግን በሙሉ አጥፍተናል” ብሎ መለሰ።