Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 15:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሳኦልም፥ “ሠራዊቱ ከአማሌቃውያን ማርከው ያመጧቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጦቹ በጎችና በሬዎች ለጌታ ለአምላክህ መሥዋዕት እንዲሆኑ ሳይገድሉ የተዉአቸው ናቸው፤ የቀሩትን ግን በሙሉ አጥፍተናል” ብሎ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሳኦልም፣ “ሰራዊቱ ከአማሌቃውያን ማርከው ያመጧቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጦቹ በጎችና በሬዎች ለእግዚአብሔር ለአምላክህ መሥዋዕት እንዲሆኑ ሳይገድሉ የተዉአቸው ናቸው፤ የቀሩትን ግን በሙሉ አጥፍተናል” ብሎ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሳኦልም “እነርሱ ወታደሮቼ ከዐማሌቃውያን የማረኩአቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጥ የሆኑትን የቀንድ ከብቶችና በጎች ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ አምጥተዋል፤ የቀሩትን ግን በሙሉ ደምስሰናል” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሳኦ​ልም፦“ሕዝቡ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠ​ዉ​አ​ቸው ዘንድ ከበ​ጎ​ችና ከላ​ሞች መን​ጋ​ዎች መል​ካም መል​ካ​ሙን አድ​ነ​ዋ​ቸ​ዋ​ልና ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን አመ​ጣን፤ የቀ​ሩ​ት​ንም ፈጽሜ አጠ​ፋሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሳኦልም፦ ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ይሠዉአቸው ዘንድ መልካሞቹን በጎችና በሬዎች አድነዋቸዋልና ከአማሌቃውያን አምጥተዋቸዋል፥ የቀሩትንም ፈጽመን አጠፋን አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 15:15
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በደሌንም በውስጤ በመሸሸግ ኃጢአቴን እንደ ሰው ሰውሬ እንደሆነ፥


ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።


እንዲህ ብሎም ወደ ቤተልሔም ላካቸው፦ “ሂዱ፤ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ” አላቸው።


እርሱ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወድዶ ኢየሱስን፦ “ባልንጀራዬስ ማን ነው?” አለው።


ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “ስማ! ትናንት ማታ ጌታ የነገረኝን ልንገርህ?” አለው። ሳኦልም፥ “ንገረኝ” ሲል መለሰለት።


ሕዝቡ ግን በጌልገላ ለአምላክህ ለጌታ ለመሠዋት ከምርኮው ከተለዩት መካከል፥ ምርጥ ምርጡን በግና በሬ ወስደዋል።”


ነገር ግን ሳኦልና ሠራዊቱ አጋግን፥ ምርጥ ምርጡን በግና የቀንድ ከብት፥ የሰባውን ጥጃና ጠቦት፥ መልካም የሆነውን ሁሉ ሳይገድሉ ተውት። እነዚህን ፈጽመው ለማጥፋት ፈቃደኞች አልነበሩም፤ ነገር ግን የተናቀውንና የማይጠቅመውን ሁሉ አጠፉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች