ዘፍጥረት 27:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄዶም አመጣ፥ ለእናቱም ሰጣት፥ እናቱም የጣፈጠውን መብል አባቱ እንደሚወደው አደረገች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ሄዶ ጠቦቶቹን ለእናቱ አመጣላት፤ እርሷም ልክ አባቱ እንደሚወድደው ዐይነት አጣፍጣ ጥሩ ምግብ አዘጋጀችለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሄዶ ጠቦቶቹን አመጣላት፤ እርስዋም ልክ አባቱ እንደሚወደው አድርጋ ጥሩ ወጥ ሠራች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄዶም አመጣ፤ ለእናቱም ሰጣት፤ እናቱም መብልን አባቱ እንደሚወድደው አደረገች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄዶም አመጣ ለእናቱም ሰጣት እናቱም የጣፈጠውን መብል አባቱ እንደሚወደው አደረገች። |