Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 25:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ይስሐቅም ዔሳው ካደነው ይበላ ነበርና ይወደው ነበር፥ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ይሥሐቅ ከዐደን የመጣ ሥጋ ደስ ይለው ስለ ነበር፣ ዔሳውን ይወድደው ነበር፤ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድደው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ዔሳው እያደነ ሥጋ ያበላው ስለ ነበረ ይስሐቅ ዔሳውን ይወድ ነበር። ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ይስ​ሐ​ቅም ዔሳ​ውን ይወድ ነበር፤ እርሱ ከአ​ደ​ነው ይበላ ነበ​ርና። ርብቃ ግን ያዕ​ቆ​ብን ትወድ ነበ​ረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ይስሐቅም ዔሳውን ይወድ ነበረ ካደነው ይበላ ነበርና፤ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 25:28
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕቆብም አባቱን አለው፦ “የበኩር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፥ እንዳዘዝኸኝ አደረግሁ፥ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና በልና ተቀመጥ፥ ካደንሁትም ብላ።”


እርሱም ደግሞ ጣፋጭ መብል አዘጋጀ፥ ለአባቱም አገባ፥ አባቱንም፦ “አባቴ ይነሣ፥ ነፍስህም ትባርከኝ ዘንድ ከልጁ አደን ይብላ” አለው።


ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅተህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ።”


እርሱም፦ “ከልጄ አደን እንድበላና ነፍሴ እንድትባርክህ አቅርብልኝ” አለ። አቀረበለትም፥ በላም፥ የወይን ጠጅ አመጣለት፥ እርሱም ጠጣ።


ወደ መንጋ ሄደህ ሁለት መልካም ጠቦቶች አምጣልኝ፥ እነርሱንም ጣፋጭ መብል ለአባትህ እንደሚወደው አደርጋለሁ፥


አሁንም ማደኛህን የፍላጻህን አፎትና ቀስትህን ውሰድ፥ ወደ ምድረ በዳም ውጣ፥ አደንም አድንልኝ፥


ሄዶም አመጣ፥ ለእናቱም ሰጣት፥ እናቱም የጣፈጠውን መብል አባቱ እንደሚወደው አደረገች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች