Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 27:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሄዶም አመጣ፤ ለእ​ና​ቱም ሰጣት፤ እና​ቱም መብ​ልን አባቱ እን​ደ​ሚ​ወ​ድ​ደው አደ​ረ​ገች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እርሱም ሄዶ ጠቦቶቹን ለእናቱ አመጣላት፤ እርሷም ልክ አባቱ እንደሚወድደው ዐይነት አጣፍጣ ጥሩ ምግብ አዘጋጀችለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሄዶም አመጣ፥ ለእናቱም ሰጣት፥ እናቱም የጣፈጠውን መብል አባቱ እንደሚወደው አደረገች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ ሄዶ ጠቦቶቹን አመጣላት፤ እርስዋም ልክ አባቱ እንደሚወደው አድርጋ ጥሩ ወጥ ሠራች፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሄዶም አመጣ ለእናቱም ሰጣት እናቱም የጣፈጠውን መብል አባቱ እንደሚወደው አደረገች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 27:14
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፤ በመ​ብ​ልና በመ​ጠጥ፥ በመ​ቀ​ማ​ጠ​ልና የዓ​ለ​ምን ኑሮ በማ​ሰብ ልባ​ች​ሁን አታ​ደ​ን​ድኑ፤ ያቺ ቀንም በድ​ን​ገት ትደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋ​ለች።


ወደ ቀኝም ተመ​ልሼ አየሁ፥ የሚ​ያ​ው​ቀ​ኝም አጣሁ፤ መሸ​ሸ​ጊ​ያም የለ​ኝም፥ ስለ ሰው​ነ​ቴም የሚ​መ​ራ​መር የለም።


እር​ሱም ደግሞ መብል አዘ​ጋጀ፥ ለአ​ባ​ቱም አመጣ፤ አባ​ቱ​ንም፥ “አባቴ ተነሥ፤ ነፍ​ስ​ህም ትባ​ር​ከኝ ዘንድ ልጅህ ከአ​ደ​ነው ብላ” አለው።


ያን የሠ​ራ​ች​ውን መብ​ልና እን​ጀ​ራ​ውን ለል​ጅዋ ለያ​ዕ​ቆብ በእጁ ሰጠ​ችው።


ወደ በጎ​ቻ​ችን ሄደህ ሁለት መል​ካም ጠቦ​ቶች አም​ጣ​ልኝ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለአ​ባ​ትህ እን​ደ​ሚ​ወ​ደው መብል አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤


“እነሆ፥ አባ​ትህ ለወ​ን​ድ​ምህ ለዔ​ሳው፦ እን​ዲህ ሲለው ሰማሁ፤ ‘ሂድና ከአ​ደ​ን​ኸው መብል አዘ​ጋ​ጅ​ተህ አም​ጣ​ልኝ፤ ሳል​ሞ​ትም በልች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ልባ​ር​ክህ።’


ሳል​ሞ​ትም ነፍሴ እን​ድ​ት​ባ​ር​ክህ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ደው መብል አዘ​ጋ​ጅ​ተህ እበላ ዘንድ አም​ጣ​ልኝ።”


ይስ​ሐ​ቅም ዔሳ​ውን ይወድ ነበር፤ እርሱ ከአ​ደ​ነው ይበላ ነበ​ርና። ርብቃ ግን ያዕ​ቆ​ብን ትወድ ነበ​ረች።


እና​ቱም አለ​ችው፥ “ልጄ ሆይ፥ መር​ገ​ምህ በእኔ ላይ ይሁን፥ ቃሌን ብቻ ስማኝ፤ ሂድና ያል​ሁ​ህን አም​ጣ​ልኝ።”


ርብ​ቃም ከእ​ር​ስዋ ዘንድ በቤት የነ​በ​ረ​ውን የታ​ላ​ቁን ልጅ​ዋን የዔ​ሳ​ውን መል​ካ​ሙን ልብስ አመ​ጣች፤ ለታ​ናሹ ልጅዋ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አለ​በ​ሰ​ችው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች