ዘዳግም 33:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ጋድም እንዲህ አለ፥ “ጋድን ሰፊ ያደረገ ቡሩክ ይሁን፥ እንደ አንበሳይቱ ዐርፎአል፥ ክንድንና ራስን ይቀጠቅጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ጋድም እንዲህ አለ፦ “የጋድን ግዛት የሚያሰፋ የተመሰገነ ነው! ክንድንና ራስን በመገነጣጠል፣ ጋድ እንደ አንበሳ በዚያ ይኖራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ጋድ ነገድም እንዲህ አለ፦ “የጋድን ግዛት ያሰፋ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ ጋድ ክንድን ወይም ግንባርን ለመስበር፥ እንደ አንበሳ ያደባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ጋድም እንዲህ አለ፦ ጋድን ሰፊ ያደረገ ቡሩክ ይሁን፤ እንደ አንበሳ ያለቆችን ክንድ ቀጥቅጦ ያርፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ጋድም እንዲህ አለ፥ 2 ጋድን ሰፊ ያደረገ ቡሩክ ይሁን፤ 2 እንደ አንበሳይቱ ዐርፎአል፤ 2 ክንድንና ራስን ይቀጠቅጣል። |
ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፥ ልጄ ሆይ፥ ከአደንህ ወጣህ፥ እንደ አንበሳ አሸመቀ፥ እንደ ሴት አንበሳም አደባ፥ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል?
ያቤጽም፦ “እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ይሁን፤ እንዳይጎዳኝም ከክፋት ጠብቀኝ” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
የጌታ ባርያ ሙሴ እንደሰጣቸው ከሌሎቹ የምናሴ ነገድ እኩሌታ ጋር የሮቤልና የጋድ ልጆች በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀበሉ።