19 በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፥ ጌታ ግን ድጋፍ ሆነኝ።
19 ወደ ሰፊ ስፍራ አወጣኝ፤ ደስ ተሰኝቶብኛልና አዳነኝ።
19 ወደ ሰፊ ቦታ አወጣኝ፤ በእኔ ደስ ስለ ተሰኘም አዳነኝ።
በተጨነቅሁ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፥ መለሰልኝ፥ አሰፋልኝም።
መከራዬን አይተሃልና፥ ነፍሴንም ከጭንቀት አድነሃታልና በምሕረትህ ደስ ይለኛል ሐሤትም አደርጋለሁ።
ለደኅንነቴም ጋሻን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም አሳደገችኝ፥
በትዕግሥት ጌታን ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኸቴንም ሰማኝ።
እንዲሁም አንተን ከመከራ ችግር ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ በወሰደህ ነበር፥ በማዕድህም ላይ ቅባት የሞላበት ምግብ በተዘጋጀ ነበር።
መንገዱን በወደደ ጊዜ፥ የሰው አካሄድ በጌታ ይጸናል።
ጌታ አምላክህ ይመስገን! እርሱ አንተን መርጦ የእስራኤል ንጉሥ በማድረግ በአንተ መደሰቱን ገልጦልሃል፤ ለእስራኤል ያለውም ፍቅር ዘላለማዊ ስለ ሆነ ጽድቅና ፍትሕ ጸንቶ እንዲኖር ታደርግ ዘንድ የእስራኤል ንጉሥ አድርጎሃል።”