Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 33:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የተሰወረውን የአሸዋውን መዝገብ፥ የባሕሩንም ባለጠግነት ይጠባሉና አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፥ በዚያ የጽድቅ መሥዋዕት ይሠዋሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤ በዚያም የጽድቅን መሥዋዕት ያቀርባሉ። በባሕሮች ውስጥ ያለውን በተትረፈረፈ ብልጽግና፣ በአሸዋውም ውስጥ የተደበቀውን ሀብት ይደሰቱበታል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሕዝቦችን ወደ ተራራ ጠርተው እዚያ ትክክለኛ የሆነውን መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ከባሕር ሀብትን፥ ከአሸዋም ድብቅ የሀብት ክምችትን ያገኛሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 አሕ​ዛ​ብን ያጠ​ፉ​አ​ቸ​ዋል፤ በዚ​ያም ይጠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ የጽ​ድቅ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ይሠ​ዋሉ፤ የባ​ሕ​ሩም ሀብት፥ በባ​ሕሩ ዳር የሚ​ኖሩ ሰዎ​ችም ገን​ዘብ ይመ​ግ​ብ​ሃ​ልና፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የተሰወረውን የአሸዋውን መዝገብ፥ 2 የባሕሩንም ባለጠግነት ይጠባሉና 2 አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤ 2 በዚያ የጽድቅ መሥዋዕት ይሠዋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 33:19
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዛብሎን በባሕር ዳር ይቀመጣል፥ እርሱም ለመርከቦች ወደብ ይሆናል፥ ዳርቻውም እስከ ሲዶና ድረስ ነው።


የምስጋና መሥዋዕትንም ይሠውለት፥ በእልልታም ሥራውን ይንገሩ።


እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።


ፍሩ፥ ኃጢአትንም አትሥሩ፥ በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ አስቡ፥ ዝምም በሉ።


የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ፥ በጌታም ታመኑ።


የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።


አንተ ታመጣቸዋለህ፥ በርስትህም ተራራ ትተክላቸዋለህ፥ ጌታ ሆይ ለማደሪያህ በሠራኸው ስፍራ፥ ጌታ ሆይ እጆችህ ባዘጋጁት መቅደስ።


ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።


የአሕዛብንም ወተት ትጠጫልሽ፥ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ እኔም ጌታ፥ የያዕቆብ ኃያል፥ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደሆንሁ ታውቂያለሽ።


በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፥ የአሕዛብም ብልጽግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፥ አይተሽ ደስ ይልሻል፥ ልብሽም ይደነቃል ይሰፋማል።


ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፦ ኑ ወደ ጌታ ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ እኛም በፍለጋው እንሄዳለን ይላሉ፤ ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የጌታ ቃል ይወጣልና።


“በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፥ የምድሩንም ፍሬ በላ፤ ከዓለትም ድንጋይ ማር፥ ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው።


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለማቅረብ፥ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ፥ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች