እግዚአብሔር ከምድሪቱ ነቃቅሎ ያስወጣቸውን የአረማውያንን ሕዝብ ልማድ በመከተል በአሕዛብ መሠዊያዎች ሁሉ ላይ ዕጣን አጠኑ፤ በዚህም ክፉ ሥራቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ፤
ዘዳግም 18:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ፥ በዚያ የሚኖሩት አሕዛብ የሚፈጽሙትን አስጸያፊ መንገድ አትከተል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ፣ በዚያ የሚኖሩት አሕዛብ የሚፈጽሙትን አስጸያፊ መንገድ አትከተል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች የሚፈጽሙትን አጸያፊ ልማድ ሁሉ አትከተል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ አሕዛብ የሚያደርጉትን ርኵሰት ታደርግ ዘንድ አትማር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ ጊዜ እነዚያ አሕዛብ የሚያደርጉትን ርኩሰት ታደርግ ዘንድ አትማር። |
እግዚአብሔር ከምድሪቱ ነቃቅሎ ያስወጣቸውን የአረማውያንን ሕዝብ ልማድ በመከተል በአሕዛብ መሠዊያዎች ሁሉ ላይ ዕጣን አጠኑ፤ በዚህም ክፉ ሥራቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ፤
ሕዝቡ ወደ ፊት እየገፋ በመጣ ጊዜ ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸውን የአሕዛብን መጥፎ ልማድ ተከተሉ፤ እንዲሁም የእስራኤል ነገሥታት ያሠራጩትን መጥፎ ልማድ ተቀባዮች ሆኑ።
ደግሞም የካህናቱ አለቆች ሁሉ ሕዝቡም እንደ አሕዛብ ያለ ርኩሰት ሁሉ በመከተል መተላለፍን አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም ጌታ ራሱ የቀደሰውን የጌታን ቤት አረከሱ።
ስለዚህ ከእናንተ በፊት በምድሪቱ ላይ የተደረገውን ጸያፍ ወግ ሁሉ ፈጽሞ እንዳታደርጉ፥ በእርሱም ራሳችሁን ፈጽሞ እንዳትረክሱ ሥርዓቴን ጠብቁ፤ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።”
አለበለዚያ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት ጊዜ የሚፈጽሟቸውን አስጸያፊ ተግባራት ሁሉ ታደርግ ዘንድ ያስተምሩሃል፤ በጌታ በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ትሠራለህ።
“ጌታ አምላክህ ከፊትህ ካስወጣቸው በኋላ፥ በልብህ፥ ‘እንድንወርሳት ወደዚች ምድር ጌታ ያስገባኝ በጽድቄ ምክንያት ነው’ አትበል፤ ጌታ እነዚህን ሕዝቦች ከፊትህ ያስወጣቸው ስለ ኃጢአታቸው ነው።
ምድራቸውን እንድትወርስ የምትገባው ስለ ጽድቅህና ስለ ልብህ ቅንነት አይደለም፥ ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔር ከፊትህ በሚያጠፋቸው በእነዚያ ሕዝቦች ኃጢአት ምክንያትና፥ ለአባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብ፥ ጌታ የማለላቸውን ቃል እንዲፈጸም ነው።