Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 18:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከቤተሰቡ ንብረት ሽያጭ ላይ ገንዘብ ቢቀበል እንኳን ባልንጀሮቹ ከሚያገኙት ጥቅም እኩል ይካፈላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከቤተ ሰቡ ንብረት ሽያጭ ላይ ገንዘብ ቢቀበል እንኳ፣ ባልንጀሮቹ ከሚያገኙት ጥቅም እኩል ይካፈላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከቤተሰብ ንብረት ሽያጭ ገንዘብ የሚቀበል ቢሆንም እንኳ እርሱም ሌሎቹ ካህናት በሚያገኙት መጠን ድርሻውን ይቀበላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከአ​ባ​ቶቹ ከብት ዋጋ ሌላ እንደ ባል​ን​ጀ​ሮቹ ከመ​ብል ድር​ሻ​ውን ይወ​ስ​ዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከተሸጠው ከአባቶቹ ከብት ዋጋ ሌላ እንደ ባልንጀሮቹ ከመብል ድርሻውን ይወስዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 18:8
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያን ቀን በይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቁርባንና ለበኵራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ።


እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፥ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፥ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።


ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋልና እነርሱ የሚሰጡአችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያው ቤት ተቀመጡ። ከቤት ወደ ቤት አትዘዋወሩ።


የጌታንም ሕግ በጽኑ እንዲያገለግሉ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የሚገባቸውን ድርሻ እንዲሰጡአቸው በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ሕዝብ አዘዘ።


ለጌታ እንደ ስጦታ አድርጎ አንድ ኅብስት ከእያንዳንዱ ቁርባን ያቀርባል። ከእርሱም የቀረው የአንድነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል።


“የምድሪቱም አሥራት ሁሉ፥ ከምድሪቱ ዘር ወይም ከዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የጌታ ነው፤ ለጌታ የተቀደሰ ነው።


ለሌዊም ልጆች፥ እነሆ፥ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች አሥራት ሁሉ ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ።


በጌታ ፊት ቆመው እንደ የሚያገለግሉት ሌዋውያን ወንድሞቹ፥ እርሱም በአምላኩ በጌታ ስም ያገልግል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች