ዘዳግም 15:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በየሰባቱ ዓመት መጨረሻ የዕዳ ምሕረት ታደርጋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየሰባቱ ዓመት መጨረሻ የዕዳ ምሕረት አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ገንዘብ ያበደርካቸውን ሰዎች ሁሉ በየሰባተኛው ዓመት መጨረሻ ላይ ዕዳቸውን በመሰረዝ ትተውላቸዋለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በየሰባቱ ዓመት የዕዳ ምሕረትን ታደርጋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በየሰባቱ ዓመት መጨረሻ የዕዳ ምሕረት ታደርጋለህ። |
‘ሰባት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፥ የተሸጠላችሁን ስድስትም ዓመት ያገለገላችሁን ዕብራዊ ወንድማችሁን እያንዳንዳችሁ አርነት ታወጡታላችሁ፥ ለእናንተም ከሚሰጠው አገልግሎት ነጻ ታደርጉታላችሁ፤’ ነገር ግን አባቶቻችሁ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም ወደ እኔ አላዘነበሉም።
አፈጻጸሙም የሚከተለው ነው፦ አበዳሪ ሁሉ ለባልጀራውም ያበደረውን ይተዋል፥ ጌታ የዕዳ ምሕረት አውጆአልና፥ ያበደረውን ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ ዕዳውን እንዲከፍለው አይጠይቀው።
‘ዕዳ የሚሠረዝበት ሰባተኛው ዓመት ተቃርቧል’ የሚል ክፉ ሐሳብ አድሮብህ፥ በችግረኛ ወንድምህ ላይ እንዳትጨክንና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር፥ እርሱም በአንተ ላይ ወደ ጌታ ጮኾ በደለኛ እንዳትሆን ተጠንቀቅ!