ዘዳግም 11:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብጽ መካከል፥ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንና በመላው አገሩ ላይ ያደረጋቸውን ምልክቶችና የሠራቸውን ነገሮች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብጽ መካከል፣ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖንና በመላው አገሩ ላይ ያደረጋቸውን ምልክቶችና የሠራቸውን ነገሮች፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተአምራቱንና እርሱ በግብጽ ንጉሥና በመላው አገሩ ላይ ያደረገውን ድንቅ ሥራ ሁሉ አይታችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግብፅም መካከል በግብፅ ንጉሥ በፈርዖንና በሀገሩ ሁሉ ላይ ያደረጋትን ተአምራቱንና ድንቅ ሥራዉን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግብፅም መካከል በንጉሡ በፈርዖንና በአገሩ ሁሉ ላይ ያደረጋትን ተአምራቱንና ሥራውን፥ |
በግብፃውያን ሠራዊት፥ በፈረሶቻቸውና በሠረገሎቻቸው ላይ፥ እናንተን ባሳደዱአችሁ ጊዜ በቀይ ባሕር ውሃ እንዴት እንዳሰጠማቸውና ጌታ ፈጽሞ እንዴት እንዳጠፋቸው አስታውሱ፤
ወይስ በፈተና፥ በተአምራት፥ በድንቅ፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራም ኃይል፥ በዐይናችሁ ፊት ጌታ አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ፥ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?
ዓይንህ ያየችውን ታላቅን መቅሠፍት፥ ምልክትንም፥ ተአምራትንም፥ ጌታ አምላክህ ሲያስወጣህ የጸናችውን እጅ፥ የተዘረጋውንም ክንድ፥ እንደዚሁ ሁሉ ጌታ አምላክህ አንተ በምትፈራቸው በሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደርጋል።