ቈላስይስ 4:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአክሪጳም፦ “በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ!” በሉልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለአርክጳም፣ “በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት ከፍጻሜ ለማድረስ ተጠንቀቅ” በሉልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአርኪጳስም “በጌታ አገልግሎት የተሰጠህን ሥራ በጥንቃቄ እንድትፈጽም” ብላችሁ ንገሩልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አክርጳንም “ከእግዚአብሔር የተሾምህባትን መልእክትህን እንድትፈጽማት ተጠንቀቅ” በሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአክሪጳም፦ በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ በሉልኝ። |
ሙሴም አሮንን፦ “ጌታ፦ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ዝም አለ።
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
ይህን ትእዛዝ ለወንድሞች ብታሳውቅ፥ በእምነትና በተከተልኸው በመልካም ትምህርት ቃላት እየተመገብክ ያደግህ፥ የክርስቶስ ኢየሱስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ።