Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 18:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በጭራሽ ዳግመኛ በእስራኤል ልጆች ላይ ቁጣ እንዳይሆንባቸው እናንተ ራሳችሁ የመቅደሱንና የመሠዊያውን ግዴታዎች ፈጽሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “በእስራኤላውያን ላይ ዳግም ቍጣ እንዳይደርስባቸው የመቅደሱና የመሠዊያው እንክብካቤ ኀላፊነት የሚመለከተው እናንተን ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ቊጣዬ በእስራኤል ሕዝብ ላይ እንደገና እንዳይገለጥ በተቀደሰው ስፍራና በመሠዊያው ላይ ያለውን የአገልግሎት ኀላፊነት የምትፈጽሙት እናንተና ልጆቻችሁ ብቻ ናችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እንደ ገና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ቍጣ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው እና​ንተ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ሕግ ጠብቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እንደ ገና በእስራኤል ልጆች ላይ ቍጣ እንዳይሆንባቸው እናንተ መቅደሱንና መሠዊያውን ጠብቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 18:5
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የጌታን ቤት አገልግሎት በሠሩ ዕድሜአቸው ሀያ ዓመትና ከዚያም ላይ በነበሩ በእያንዳንዳቸው በስማቸው በተቆጠሩት ላይ የአባቶች ቤት አለቆች የሆኑት በየአባቶቻቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነዚህ ነበሩ።


ለጌታም ቤት አገልግሎት የመገናኛውን ድንኳን ሥርዓት የመቅደሱንም ሥርዓት የወንድሞቻቸውንም የአሮንን ልጆች ሥርዓት በመጠበቅ ያገለግሉ ነበረ።”


ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የመቅደሱና በእግዚአብሔር የተሾሙ አለቆች ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ።


የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱም ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፥ አባቶቻቸውም የጌታን ሰፈር መግቢያ ይጠብቁ እንደ ነበር እንዲሁ የድንኳኑን የመግቢያ ደጅ ይጠብቁ ነበር።።


እነርሱና ልጆቻቸውም በጌታ ቤት በድንኳኑ ደጆች ላይ ዘበኞች ነበሩ።


ከሌዋውያንም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን እነዚህ ናቸው፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረና ያለ ሌላ ሥራ በየእልፍኛቸው ይቀመጡ ነበር።


ከመጋረጃው ውጭ ባለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በጌታ ፊት ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ በትውልዳቸው የዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።”


ስለዚህ ስለ ነብያት የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኩሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና፥ እሬትን አበላቸዋለሁ የሐሞትንም ውኃ አጠጣቸዋለሁ።”


የእስራኤል ልጆች ከእኔ በራቁ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዓት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ሊያገለግሉኝ ወደ እኔ ይቀርባሉ፤ ስቡንና ደሙን ወደ እኔ ሊያቀርቡ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ወደ መቅደሴም ይገባሉ እኔን ለማገልገል ወደ ገበታዬ ይቀርባሉ ሥርዓቴን ይጠብቃሉ።


ሙሴም አሮንን፥ ልጆቹንም አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እንዳትሞቱ በማኅበሩም ሁሉ ላይ እርሱ እንዳይቈጣ የራሳችሁን ጠጉር አታጐስቁሉ፥ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፤ ጌታ እሳትን ልኮ ስላደረገው ማቃጠል ግን ወንድሞቻችሁ የእስራኤል ቤት ሁሉ ያልቅሱ።


አሮን ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከምስክሩ መጋረጃ ውጭ በጌታ ፊት ሁልጊዜ ያዘጋጀው፤ ለዘለዓለም ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ይሁን።


ቁጣዬ በእረኞች ላይ ነዷል፥ መሪዎችንም እቀጣለሁ፤ የሠራዊት ጌታም የይሁዳን ቤት መንጋውን ጐብኝቶአል፥ በውጊያ ላይ ክብር እንደተቀዳጀ ፈረስ ያደርጋቸዋል።


ነገር ግን በምስክሩ ማደሪያና በዕቃው ሁሉ የእርሱም በሆነው ነገር ሁሉ ላይ ሌዋውያንን ሹማቸው። ማደሪያውንና ዕቃዎቹን ሁሉ ይሸከሙ፥ ያገልግሉትም፥ በማደሪያውም ዙሪያ ይስፈሩ።


ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ጉባኤ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ሌዋውያን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይስፈሩ፤ ሌዋውያንም የምስክሩን ማደሪያ ይጠብቁ።”


ሙሴም አሮንን እንዲህ አለው፦ “ጥናህን ውሰድ፥ ከመሠዊያውም ላይ እሳት አድርግበት፥ ዕጣንም ጨምርበት፥ ወደ ማኅበሩም ፈጥነህ ውሰደው አስተስርይላቸውም፤ ከጌታ ዘንድ ቁጣ ወጥቶአልና መቅሠፍት ጀምሮአል።”


ነገር ግን ከእናንተ ጋር በአንድነት ይሁኑ፥ ለድንኳኑም አገልግሎት ሁሉ የመገናኛውን ድንኳን ግዴታዎች ይፈጽሙ፤ ሌላም ሰው ወደ እናንተ አይቅረብ።


“የቀዓትን ወገኖች ነገድ ከሌዋውያን መካከል አታጥፉአቸው፤


የእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደሱ በቀረቡ ጊዜ መቅሠፍት እንዳያገኛቸው፥ ለእስራኤል ልጆች እንዲያስተስርዩላቸው፥ የእስራኤልንም ልጆች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲሠሩ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአቸዋለሁ።”


“ለአሮን ንገረው እንዲህም በለው መብራቶቹን ስትለኩስ ሰባቱ መብራቶች በመቅረዙ ፊት ያበራሉ።”


ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! አስቀድሞ ስለ አንተ የተነገረውን ትንቢት ሁሉ መሠረት በማድረግ፥ በእነርሱ መልካም ውጊያን እንድትዋጋ ይህችን ትእዛዝ በአደራ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤


ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብዘገይ ግን፥ በዚህ በጻፍሁልህ ትእዛዝ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነችው በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድታውቅ ነው።


አንዱን ከሌላው በማበላለጥ ምንም ዓይነት ነገር ሳታደርግ፥ ያለ አድልዎ እነዚህን ትዛዛቶች እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ በተመረጡትም መላእክት ፊት አደራ እልሃለሁ።


ጢሞቴዎስ ሆይ! በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች