Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ጢሞቴዎስ 6:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጢሞቴዎስ ሆይ! በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ጢሞቴዎስ ሆይ፤ በዐደራ የተቀበልኸውን ሁሉ ጠብቅ፤ እግዚአብሔርን ከማያስከብር ከከንቱ ልፍለፋና ለተቃውሞ በውሸት ዕውቀት ከተባለ ፍልስፍና ራቅ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ጢሞቴዎስ ሆይ! በዐደራ የተሰጠህን ጠብቅ፤ ዕውቀት ሳይሆን “ዕውቀት” ከሚመስለው ነገር ልፍለፋ ራቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጢሞቴዎስ ሆይ! በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ጢሞቴዎስ ሆይ፥ በውሸት እውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ፥ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ጢሞቴዎስ 6:20
30 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን እንደ ሰው ወግና እንደ መሠረታዊው የዓለም ረቂቅ መንፈስ በፍልስፍናና በከንቱ መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ።


ነገር ግን ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍ ራቅ፤ ምክንያቱም ሰዎችን ከፊት ይልቅ ወደ ኃጢአት ይመራልና፤


ራስን ማዋረድና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባየውም ራእይ ላይ በጽኑ እየተመረኮዘ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ፤


በማንኛውም መንገድ ጥቅሙ ብዙ ነው። አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃላት አደራ ተሰጣቸው።


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ይህን ትእዛዝ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ጠብቅ፤


ስለዚህም ወንድሞች ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ትውፊት ያዙ።


ነገር ግን ሞኝነት ካለው ውዝግብና ከትውልዶች ታሪክ ከመከፋፈልም ስለ ሕግም ከሚሆን ጠብ ራቅ፤ የማይጠቅሙና ከንቱዎች ናቸውና፤


እንግዲህ ልጄ ሆይ! አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ።


ይህም ትምህርት ለእኔ በአደራ ከተሰጠኝ ከብሩክ እግዚአብሔር ክቡር ወንጌል ጋር የሚስማማ ነው።


ስለዚህ በምትታገሱት መከራችሁና በስደታችሁ ሁሉ ስለ እናንተ መጽናትና እምነት እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት በእናንተ እንመካለን።


በአይሁድ ተረቶችና እውነትን በማይቀበሉ በሰዎች ትእዛዛት እንዳይጠመዱ ነው።


እውነተኛውንም ትምህርት ለመምከርና ተቃዋሚዎቹን ለመገሠጽ እንዲችል፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና።


የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! አንተ ግን ከእነዚህ ነገሮች ሽሽ፤ ጽድቅን፥ እግዚአብሔርን መምሰልን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ መጽናትን፥ የዋህነትን ግን ተከተል።


ነገር ግን ከረከሰው ከዚህ ዓለም አፈ ታሪክና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አለማምድ።


አንዳንድ ሰዎች ከእነዚህ ነገሮች ፈቀቅ ብለው ወደ ከንቱ ንግግር በመሄድ፥


ራሳቸውንም በተረት፥ መጨረሻም በሌለው የትውልዶች ታሪክ እንዳይጠመዱ እንድታዝ ለመንሁህ፤ ሆኖም ግን እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ከንቱ ምርምር ያመጣሉ እንጂ በእምነት የሚገኝውን የእግዚአብሔርን መጋቢነት አይጠቅሙም።


የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞኝነት ነው። እንደተጻፈውም፥ “እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል፤”


የአቴና ሰዎች ሁሉና በዚያ የኖሩ እንግዶች አዲስ ነገርን ከመናገርና ከመስማት በቀር በሌላ ጉዳይ አይውሉም ነበርና።


ከኤፊቆሮስ ወገንና ኢስጦኢኮችም ከተባሉት ፈላስፎች አንዳንዶቹ ከእርሱ ጋር ተገናኙ። አንዳንዶቹም “ይህ ለፍላፊ ምን ሊናገር ይወዳል?” አሉ፤ ሌሎችም የኢየሱስንና የትንሣኤውን ወንጌል ስለ ሰበከላቸው “አዲሶችን አማልክት የሚያወራ ይመስላል፤” አሉ።


እንግዲህ ቃሉን እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስታውስ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ። ባትነቃ ግን እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፤ በማናቸውም ሰዓት እንደምመጣብህ ከቶ አታውቅም።


የጋራ በሆነው እምነት እውነተኛ ልጄ ለሆንከው ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከአዳኛችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ሰላም ይሁን።


በዐዋቂዎች መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፤ ይሁን እንጂ የዚህን ዓለም ወይም መጨረሻቸው ጥፋት የሚሆነውን የዚህን ዓለም ገዢዎች ጥበብ አይደለም፤


ጥበበኞች ነን ሲሉ ሞኞች ሆኑ፤


ወደ ደርቤንና ወደ ልስጥራንም ደረሰ። እነሆም፥ በዚያ የአንዲት ያመነች አይሁዳዊት ልጅ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀመዝሙር ነበረ፤ አባቱ ግን የግሪክ ሰው ነበረ።


በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከጌታችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።


ይህንንም በመረዳት ሕግ የተሠራው ለጻድቃን ሳይሆን ይልቁንስ ለበደለኞችና ለማይታዘዙ፥ ለዐመጸኞችና ለኀጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና ለርኩሳን፥ አባትና እናትን ለሚገድሉ፥ ለነፍሰ ገዳዮች፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች