Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ጢሞቴዎስ 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሽማግሌዎች እጃቸውን በአንተ ላይ የጫኑ ጊዜ በትንቢት የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሽማግሌዎች እጃቸውን በአንተ ላይ ሲጭኑ በትንቢት የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ትንቢት በተነገረልህ ጊዜና የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችም እጃቸውን በጫኑብህ ጊዜ የተሰጠህን በአንተ ያለውን መንፈሳዊ ስጦታ አትዘንጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በትንቢት ከሽማግሌዎች እጅ መጫን ጋር የተሰጠህን፥ በአንተ ያለውን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ጢሞቴዎስ 4:14
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲህም ደግሞ አደረጉ፤ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ላኩት።


በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱአቸው።


ጳውሎስም እጁን በጫነባቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው፤ በልሳኖችም ተናገሩ፤ ትንቢትም ተናገሩ።


እንዲህም ሊቀ ካህናቱ ደግሞ ሽማግሌዎቹም ሁሉ ይመሰክሩልኛል፤ ከእነርሱ ደግሞ መልእክትን ለወንድሞቻቸው ተቀብዬ፥ በደማስቆ ያሉትን ደግሞ ታስረው እንዲቀጡ ወደ ኢየሩሳሌም ላመጣ ወደዚያ እሄድ ነበር።


በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፤ ከጸለዩም በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።


በዚያን ጊዜ እጃቸውን ጫኑባቸው፤ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ።


ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! አስቀድሞ ስለ አንተ የተነገረውን ትንቢት ሁሉ መሠረት በማድረግ፥ በእነርሱ መልካም ውጊያን እንድትዋጋ ይህችን ትእዛዝ በአደራ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤


እድገትህ በሁሉ ሰው ፊት እንዲገለጥ እነዚህን ነገሮች በጥንቃቄ በሥራ ላይ አውል፤ ለእነርሱም ራስህን ሙሉ በሙሉ በመስጠት ትጋ።


በመልካም የሚያስተዳድሩ፥ በተለይም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙ ሽማግሌዎች፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።


በሁለት ወይም በሦስት ምስክር ካልተደገፈ በቀር በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል።


በማንም ላይ ፈጥነህ እጆችህን አትጫን፤ በሌሎችም ኃጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽህና ጠብቅ።


መልካሙን የእምነት ውጊያ ተዋጋ፤ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የመሰከርህለትን የዘለዓለምን ሕይወት ያዝ።


በዚህም ምክንያት እጆቼን ስጭን የተሰጠህን በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታቀጣጥል አሳስብሃለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች