ነገር ግን በጣም ያዘነች ነፍስ፥ አጎንብሳ የምትሄድና አቅም ያነሳት፥ የፈዘዙ ዐይኖችና የተራበች ነፍስ፥ ክብርን ወይም ተገቢውን ነገር ለጌታ ይሰጣሉ።
ነገር ግን አዝናና ተጨንቃ የምትኖር፥ በብዙ መከራም ያዘነች ሰውነትና የፈዘዙ ዐይኖች፥ የተራበችም ነፍስ ያመሰግኑሃል፤ አቤቱ ለጽድቅህም ይገዛሉ።