አሞጽ 7:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም፥ መከር ካለፈ በኋላ ያለው እህል በሚበቅልበት መጀመሪያ ላይ አንበጣን ፈጠረ፤ እነሆም፥ ከንጉሡ አጨዳ በኋላ ማንም ሰው ሳይዘራው የበቀለ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር ይህን አሳየኝ፤ የንጉሡ የመኸር እህል ከተሰበሰበ በኋላ ገቦው መብቀል በጀመረ ጊዜ፣ እርሱ የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ እግዚአብሔር ይህን ራእይ አሳየኝ፤ እነሆ የንጉሡ የመከር እህል ከታጨደ በኋላ እንደገና ገቦ ሆኖ በበቀለው እህል ላይ እግዚአብሔር የአንበጣ መንጋ እንዲፈለፈል አደረገ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፤ እነሆም ከምሥራቅ አንበጣ ይመጣል፤ አንዱም ኵብኵባ ንጉሡ ጎግ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አሳየኝ፥ እነሆም፥ የኋለኛው ሣር በሚበቅልበት መጀመሪያ ላይ አንበጣን ፈጠረ፥ እነሆም፥ ከንጉሡ አጨዳ በኋላ የበቀለ የገቦ ነበረ። |
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችን ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው በኋላ፥ ጌታ አሳየኝ፥ እነሆም፥ በጌታ መቅደስ ፊት ሁለት ቅርጫት በለስ ተቀምጠው ነበር።
“በዋግና በአረማሞ መታኋችሁ፤ የአታክልቶቻችሁንም ብዛት ወይኖቻችሁንም በለሶቻችሁንም ወይራዎቻችሁንም ተምች በላው፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።