Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 33:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አንበጣ እንደሚሰበሰብ ምርኮአችሁ ትሰብስባለች፤ ኩብኩባም እንደሚዘል ሰዎች ይዘልሉበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ሕዝቦች ሆይ፤ አንበጣ እንደሚሰበስብ ብዝበዛችሁም ይሰበሰባል፤ ሰዎችም እንደ ኵብኵባ ይጨፍሩበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 አንበጣ እንደሚሰበሰብ ምርኮ ይሰበሰባል፤ ኩብኩባዎች እንደሚዘሉ ሰዎች በምርኮው ላይ ይረባረባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አን​በጣ እን​ደ​ሚ​ሰ​በ​ሰብ ትን​ሹም ትል​ቁም ምር​ኮ​አ​ችሁ እን​ዲሁ ይሰ​በ​ሰ​ብ​ላ​ች​ኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አንበጣ እንደሚሰበሰብ ምርኮአችሁ ትሰበሰባለች፥ ኩብኩባም እንደሚዘልል ሰዎች ይዘልሉበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 33:4
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሰደድሁባችሁ ታላቁ ሠራዊቴ አንበጣና ደጎብያ ኩብኩባና ተምች የበላቸውን ዓመታት እመልስላችኋለሁ።


በከተማም ያኰበኩባሉ፥ በቅጥሩም ላይ ይሮጣሉ፥ ወደ ቤቶችም ይወጣሉ፥ እንደ ሌባም በመስኮቶች ይገባሉ።


ገመዶችህ ላልተዋል፥ ችካላቸውንም አልጸናም፥ ሸራውንም መወጠር አልቻሉም። በዚያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ሀብት ይከፋፈላል፤ አንካሶች እንኳ ከክፍፍሉ ይደርሳቸዋል።


ኢዮሣፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ለመውሰድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፥ በዘበዙትም፥ ሁሉንም ለመሸከም አልቻሉም፤ ከምርኮውም ብዛት የተነሣ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ይበዘብዙ ነበር።


አሳም ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው፤ ኢትዮጵያውያንም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ወደቁ፥ በጌታና በሠራዊቱ ፊት ተሰባብረዋልና፤ የይሁዳ ሰዎችም እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ።


ከፍጅት ድምፅ ሕዝቦች ሸሹ፤ በመነሣትህም መንግሥታት ተበተኑ።


ጌታም በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፤ ጽዮንን በፍትህና በጽድቅ ሞላት።


ስለዚህ እነሆ እጄን በአንተ ላይ ዘርግቻለሁ፥ እንዲበዘብዙህ ለሕዝቦች እሰጥሃለሁ፥ ከሕዝቦች እቆርጥሃለሁ፥ ከአገሮችም እደመስስሃለሁ፤ አጠፋሃለሁም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃለህ።


ከተምች የቀረውን አንበጣ በላው፥ ከአንበጣም የቀረውን ደጎብያ በላው፥ ከደጎብያም የቀረውን ኩብኩባ በላው።


እሳት በፊታቸው ትባላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፥ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ዔድን ገነት፥ በኋላቸውም የምድረ በዳ በረሃ ናት፥ ከእነርሱም የሚያመልጥ የለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች