2 ሳሙኤል 22:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንደጽድቄ፥ በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና ብድራትን ከፈለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፣ በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና ብድራትን ከፈለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና ዋጋዬን ከፈለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና በዐይኖቹ ፊት መለሰልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና በዓይኖቹ ፊት መለሰልኝ። |
ሰሎሞንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አገልጋይህ የነበረው አባቴ ዳዊት ደግ፥ ታማኝና ቅን ሰው በመሆኑ ጽኑ ፍቅርህን ስታሳየው ኖረሃል፤ ዛሬም በእርሱ እግር ተተክቶ በዙፋኑ የሚቀመጥ ልጅ በመስጠት ታላቅና ጽኑ የሆነውን የማያቋርጥ ፍቅርህን ገልጠህለታል።
ጌታ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ጽድቁና እንደ ታማኝነቱ ይክፈለው። እኔ ግን ዛሬ አንተን ጌታ በእጄ አሳልፎ ሰጥቶኝ ሳለ ጌታ በቀባው ላይ እጄን አላነሣሁም።