አዳምንም ካስወጣው በኋላ፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በሁሉም አቅጣጫ የምትውለበለብ ነበልባላዊ ሰይፍን በዔድን ገነት በስተ ምሥራቅ አስቀመጠ።
2 ሳሙኤል 22:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ ሲከንፍ ታየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፍ መጠቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኪሩቤል ላይ ሆኖ በረረ፤ በነፋስም ክንፎች ላይ ሆኖ መጠቀ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፤ በነፋስም ክንፎች ሆኖ ታየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኪሩብም ላይ ተቀምቶ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ ሆኖ ታየ፥ |
አዳምንም ካስወጣው በኋላ፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና በሁሉም አቅጣጫ የምትውለበለብ ነበልባላዊ ሰይፍን በዔድን ገነት በስተ ምሥራቅ አስቀመጠ።
ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ፥ በኪሩቤል ላይ በተቀመጠ በሠራዊት ጌታ ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው በዓል ሄዱ።
የእስራኤልም አምላክ ክብር በላዩ ላይ አርፎ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መግቢያ ሄዶ ነበር፥ በፍታ የለበሰውን በወገቡም የጸሐፊ ቀለም ቀንድ የያዘውን ሰው ጠራ።
ስለዚህ ሕዝቡ ሰዎችን ወደ ሴሎ ልከው፥ በኪሩቤል መካከል በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውን የሠራዊት ጌታን የኪዳን ታቦት አስመጡ፤ ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስ ከኪዳኑ ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።