ሕዝቅኤል 9:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 የእስራኤልም አምላክ ክብር በላዩ ላይ አርፎ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መግቢያ ሄዶ ነበር፥ በፍታ የለበሰውን በወገቡም የጸሐፊ ቀለም ቀንድ የያዘውን ሰው ጠራ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 በዚህ ጊዜ የእስራኤል አምላክ ክብር ከነበረበት ከኪሩብ በላይ ተነሥቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መድረክ ሄደ። እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውን በጐኑም የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር ያነገበውን ሰው ጠራ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ከዚህ በኋላ የእስራኤልን አምላክ ክብር የሚገልጥ ነጸብራቅ ቀድሞ ካረፈበት ከኪሩብ ላይ ተነሥቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ሄደ፤ እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውንና የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር የያዘውን ሰው፥ ጠራው፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄዶ ነበር፤ በፍታም የለበሰውን፥ የሰንፔር መታጠቂያም በወገቡ የታጠቀውን ሰው ጠራ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄዶ ነበር፥ በፍታ የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ። ምዕራፉን ተመልከት |