Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 68:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጽኑ ተራራዎች ሆይ ለምን በቅናት ታያላችሁ? እግዚአብሔር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው፥ በእውነት ጌታ ለዘለዓለም ያድርበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የእግዚአብሔር ሠረገላዎች እልፍ አእላፍ ናቸው፤ ሺሕ ጊዜም ሺሕ ናቸው፤ ጌታ ከሲና ወደ መቅደሱ ገባ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “እግዚአብሔር በብዙ ሺህ ከሚቈጠሩት ታላላቅ ሠረገላዎች ጋር ከሲና ወደ ተቀደሰው መቅደሱ ይመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከባ​ሪ​ያ​ህም ፊት​ህን አት​መ​ልስ፤ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና ፈጥ​ነህ ስማኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 68:17
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ የእሳት ፈረሶች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት በመካከላቸው ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ።


ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም፥ ጨለማ ከእግሩ በታች ነበረ።


በጽዮን ለሚኖር ለጌታ ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል ድንቅ ሥራውን ንገሩ፥


እርሱም “ወደዚህ አትቅረብ፤ ጫማህን ከእግርህ አውልቅ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ መሬት ነውና” አለው።


በዘመኑም ፍጻሜ፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራ ከተራሮች ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ ኰረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ።


እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘለዓለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ ማሳረፊያ ይህ ነው። የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በዝሙታቸውና በከፍታዎቻቸው ባለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ዳግመኛ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም።


አሁንም ዝሙታቸውንና የነገሥታቶቻቸውን ሬሳ ከእኔ ዘንድ ያርቁ፥ እኔም ለዘለዓለም በመካከላቸው እኖራለሁ።


ጌታ ሆይ ንዴትህ በወንዞች ላይ ነውን? ወይስ ቁጣህ በወንዞች ላይ ወይም መዓትህ በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህ፥ በማዳን ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና።


ወይስ አባቴን ብለምነው ከዐሥራ ሁለት ጭፍሮች የሚበዙ መላእክት አሁን ሊልክልኝ የማይችል ይመስልሃልን?


እንዲህም አለ፦ “ጌታ ከሲና ተራራ መጣ፥ በሴይርም እንደ ንጋት ተገለጠ፥ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፥ በስተቀኙም ከእሳት ነበልባል ጋር፥ ከአእላፋት ቅዱሳኑም ጋር መጣ።


አየሁም፤ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቁጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፤


የፈረሰኞችም ጭፍራ ቍጥር ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበረ፤ ቁጥራቸውን ሰማሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች