የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 21:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንደገና በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤል መካከል ጦርነት ተደረገ። ዳዊትም ከሰዎቹ ጋር ሆኖ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወረደ፤ ዳዊትም ደከመው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንደ ገና በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤል መካከል ጦርነት ተደረገ። ዳዊትም ከሰዎቹ ጋራ ሆኖ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወረደ፤ በዚያም ደከመው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤላውያን መካከል የተደረገ ሌላም ጦርነት ነበር፤ ስለዚህም ዳዊትና ተከታዮቹ ዘምተው ፍልስጥኤማውያንን ወጉ፤ ከውጊያዎቹም በአንዱ ዳዊት ደክሞት ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መካ​ከል ደግሞ ጦር​ነት ሆነ፤ ዳዊ​ትም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር አገ​ል​ጋ​ዮቹ ወረዱ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ተዋጉ፤ ዳዊ​ትም ደከመ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤልም መካከል ደግሞ ሰልፍ ነበረ፥ ዳዊትም ከእርሱም ጋር ባሪያዎቹ ወረዱ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ተዋጉ፥ ዳዊትም ደከመ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 21:15
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢበኖብ የተባለ ዳዊትን ለመግደል አሰበ። የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ።


ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፥ ፍልስጤማውያን ሁሉ ዳዊትን ለመፈለግ በሙሉ ኀይላቸው ወጡ፤ ዳዊት ግን ይህን ሰምቶ ወደ ምሽጉ ወረደ።


ፍልስጥኤማውያን እንደገና መጥተው በራፋይም ሸለቆ ተበታትነው ሰፈሩ።


ስለዚህም ዳዊት ጌታ እንዳዘዘው አደረገ፤ ፍልስጥኤማውያንንም ከገባዖን እስከ ጌዜር ድረስ መታቸው።


ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው፤ በቁጥጥሩም ሥር አደረጋቸው፥ ሜተግ አማ የተባለችውንም ከተማ ዳዊት ከፍልስጥኤማውያን እጅ ወሰደ።


ከዚህም በኋላ በጌዝር ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ተደረገ፤ ኩሳታዊውም ሴቦካይ ከራፋይም ወገን የነበረውን ሲፋይን ገደለ። ፍልስጥኤማውያንም ተሸነፉ።


እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ፥ ለሚመጣ ትውልድም ሁሉ ክንድህን ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ፥ አቤቱ፥ አትተወኝ።


በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፥ ጉልበቴም ባለቀ ጊዜ አትተወኝ።


ልቤና ሥጋዬ አለቀ፥ እግዚአብሔር ግን ዘለዓለም የልቤ ኃይልና እድል ፈንታዬ ነው።


ቤት ጠባቆች በሚንቀጠቀጡበት፥ ኃያላን ሰዎችም በሚጎብጡበት፥ ጥቂቶች ሆነዋልና ፈጭታዎች ሥራ በሚፈቱበት፥ በመስኮትም ሆነው የሚመለከቱ በሚጨልሙበት፥ በአደባባይም ደጆቹ በሚዘጉበት ቀን፥