Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 21:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መካ​ከል ደግሞ ጦር​ነት ሆነ፤ ዳዊ​ትም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር አገ​ል​ጋ​ዮቹ ወረዱ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጋር ተዋጉ፤ ዳዊ​ትም ደከመ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እንደ ገና በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤል መካከል ጦርነት ተደረገ። ዳዊትም ከሰዎቹ ጋራ ሆኖ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወረደ፤ በዚያም ደከመው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እንደገና በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤል መካከል ጦርነት ተደረገ። ዳዊትም ከሰዎቹ ጋር ሆኖ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወረደ፤ ዳዊትም ደከመው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤላውያን መካከል የተደረገ ሌላም ጦርነት ነበር፤ ስለዚህም ዳዊትና ተከታዮቹ ዘምተው ፍልስጥኤማውያንን ወጉ፤ ከውጊያዎቹም በአንዱ ዳዊት ደክሞት ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤልም መካከል ደግሞ ሰልፍ ነበረ፥ ዳዊትም ከእርሱም ጋር ባሪያዎቹ ወረዱ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ተዋጉ፥ ዳዊትም ደከመ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 21:15
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቤት ጠባ​ቆች በሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀ​ጡ​በት፥ ኀያ​ላን ሰዎ​ችም በሚ​ጐ​ብ​ጡ​በት፥ ጥቂ​ቶች ሆነ​ዋ​ልና ፈጭ​ታ​ዎች ሥራ በሚ​ፈ​ቱ​በት፥ በመ​ስ​ኮ​ትም ሆነው የሚ​መ​ለ​ከቱ በሚ​ጨ​ል​ሙ​በት፥


በፊ​ቱም ኢት​ዮ​ጵያ ይሰ​ግ​ዳሉ፥ ጠላ​ቶ​ቹም አፈ​ርን ይል​ሳሉ።


ከዚ​ህም በኋላ በጋ​ዜር ላይ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ጦር​ነት እንደ ገና ሆነ፤ ያን​ጊ​ዜም ኡሳ​ታ​ዊው ሴቦ​ቃይ ከኀ​ያ​ላን ወገን የነ​በ​ረ​ውን ሲፋ​ይን ገድሎ ጣለው።


ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረገ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም እስከ ጌሴራ ድረስ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ደግሞ መጡ፤ ወደ ረዓ​ይ​ትም ሸለቆ ወረዱ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዳዊት በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ እንደ ተቀባ ሰሙ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ዳዊ​ትን ሊፈ​ልጉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም በሰማ ጊዜ ወደ ምሽጉ ወረደ።


ብቻ​ውን ተአ​ም​ራ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።


ከራ​ፋ​ይም ወገን የነ​በ​ረው ኤስቢ መጣ፤ የጦ​ሩም ሚዛን ክብ​ደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣ​ሪ​ያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊ​ት​ንም ሊገ​ድ​ለው ፈለገ።


ከዚ​ህም በኋላ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን መታ፤ አዋ​ረ​ዳ​ቸ​ውም፤ ዳዊ​ትም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ምር​ኮን ወሰደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች