2 ሳሙኤል 21:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአያ ልጅ ሪጽፋ ማቅ ወስዳ፥ በቋጥኝ ላይ ለራሷ አነጠፈች፤ ከመከር ወቅት መጀመሪያ አንሥቶ ዝናብ ከሰማይ በሬሳዎቹ ላይ እስከወረደ ጊዜ ድረስ ቀን የሰማይ ወፎች ሌሊት የዱር አራዊት እንዲነኳቸው አልፈቀደችም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ ማቅ ወስዳ፣ በቋጥኝ ላይ ለራሷ አነጠፈች፤ ከመከር ወቅት መጀመሪያ አንሥቶ ዝናብ ከሰማይ በሬሳዎቹ ላይ እስከ ወረደ ጊዜ ድረስ፣ ቀን የሰማይ ወፎች ሌሊት የዱር አራዊት እንዲነኳቸው አልፈቀደችም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የሳኦል ቊባት የነበረችው የአያ ልጅ ሪጽፋ ሬሳዎቹ ባሉበት ስፍራ አጠገብ በሚገኘው ቋጥኝ ድንጋይ ላይ ማቅ ዘርግታ ከስሩ ተቀመጠች፤ እርስዋም ከመከር ጊዜ መጀመሪያ አንሥቶ ዝናብ እስከሚጥልበት ጊዜ ድረስ እዚያ ቈየች፤ ቀን ቀን ወፎች በሬሳዎቹ ላይ እንዳያርፉ እየተከላከለች፥ ሌሊት ሌሊትም አውሬ እንዳይበላቸው ትጠብቃቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኢዮሔል ልጅ ሩጻፋም ማቅ ወስዳ ከመከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰማይ እስኪዘንብ ድረስ በድንጋይ ላይ ዘረጋችው፤ በቀንም የሰማይ ወፎች፥ በሌሊትም የዱር አራዊት ያርፉባቸው ዘንድ አልተወችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢዮሄልም ልጅ ሪጽፋ ማቅ ወስዳ ከመከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰማይ እስኪዘንብ ድረስ በድንጋይ ላይ ዘረጋችው በቀንም ወፎች በሌሊትም አራዊት ያርፉባቸው ዘንድ አልተወችም። |
ሳኦልም ሪጽፋን የምትባለውን የአያን ልጅ በዕቁባትነት አስቀምጦአት ነበር፤ ኢያቡስቴም አበኔርን፥ “ለምንድን ነው ከአባቴ ዕቁባት ጋር የተኛኸው?” አለው።
የእስራኤልም ልጆች ተሰለፉ፥ ሊገጥሙአቸውም ወጡ፥ የእስራኤልም ልጆች እንደ ሁለት ትናንሾች የፍየል መንጋዎች ሆነው በፊታቸው ሰፈሩ፥ ሶርያውያን ግን ምድሩን ሞልተው ነበር።
በውኑ በአሕዛብ ከንቱ ጣዖታት መካከል ዝናብን ሊያዘንብ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ካፊያን መስጠት ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ! አንተ አይደለህምን? አንተ እነዚህን ሁሉ ነገሮች አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።
አንተ፥ ወታደሮችህና ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ ሁሉ በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ፤ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።
እኛም እንወቅ፤ ጌታን ለማወቅ እንትጋ፤ እንደ ንጋትም መገለጡ እርግጥ ነው፤ እንደ ዝናብ ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ በልግ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።”
እናንተ የጽዮን ልጆች፥ ጌታ አምላካችሁ ቀድሞ የሚደርሰውን ዝናብ ስለ ጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ በፊትም ቀዳሚውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ።
የበልግ ዝናብ እንዲሰጣች ጌታን ለምኑ፤ መብረቁን ደመና የሚያደርግ ጌታ፥ ያደርጋል፥ እርሱም ለእያንዳንዱ የምድር ተክል የሚሆን ዝናብ ይሰጣል።
ስትማረክ የለበሰችውንም ልብስ ታውልቅ፤ እቤትህ ተቀምጣ ለአባትና ለእናቷ ወር ሙሉ ካለቀሰችላቸው በኋላ፥ ልትደርስባትና ባል ልትሆናት፥ እርሷም ሚስት ልትሆንህ ትችላለች።
በድኑን በዕንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድረው፤ ምክንያቱም በዕንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፤ አምላክህ ጌታ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ በዚያኑ ዕለት ቅበረው።”
ጌታ ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እኔ መትቼ እጥልሃለሁ፤ ራስህንም እቆርጠዋለሁ። በዚህች ዕለት የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ሬሣ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፤ ዓለምም ሁሉ በእስራኤል ዘንድ እግዚአብሔር መኖሩን ያውቃል።