Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 21:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዚህ በኋላ የሳኦል ቊባት የነበረችው የአያ ልጅ ሪጽፋ ሬሳዎቹ ባሉበት ስፍራ አጠገብ በሚገኘው ቋጥኝ ድንጋይ ላይ ማቅ ዘርግታ ከስሩ ተቀመጠች፤ እርስዋም ከመከር ጊዜ መጀመሪያ አንሥቶ ዝናብ እስከሚጥልበት ጊዜ ድረስ እዚያ ቈየች፤ ቀን ቀን ወፎች በሬሳዎቹ ላይ እንዳያርፉ እየተከላከለች፥ ሌሊት ሌሊትም አውሬ እንዳይበላቸው ትጠብቃቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ ማቅ ወስዳ፣ በቋጥኝ ላይ ለራሷ አነጠፈች፤ ከመከር ወቅት መጀመሪያ አንሥቶ ዝናብ ከሰማይ በሬሳዎቹ ላይ እስከ ወረደ ጊዜ ድረስ፣ ቀን የሰማይ ወፎች ሌሊት የዱር አራዊት እንዲነኳቸው አልፈቀደችም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የአያ ልጅ ሪጽፋ ማቅ ወስዳ፥ በቋጥኝ ላይ ለራሷ አነጠፈች፤ ከመከር ወቅት መጀመሪያ አንሥቶ ዝናብ ከሰማይ በሬሳዎቹ ላይ እስከወረደ ጊዜ ድረስ ቀን የሰማይ ወፎች ሌሊት የዱር አራዊት እንዲነኳቸው አልፈቀደችም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የኢ​ዮ​ሔል ልጅ ሩጻ​ፋም ማቅ ወስዳ ከመ​ከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰ​ማይ እስ​ኪ​ዘ​ንብ ድረስ በድ​ን​ጋይ ላይ ዘረ​ጋ​ችው፤ በቀ​ንም የሰ​ማይ ወፎች፥ በሌ​ሊ​ትም የዱር አራ​ዊት ያር​ፉ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ተ​ወ​ችም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የኢዮሄልም ልጅ ሪጽፋ ማቅ ወስዳ ከመከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰማይ እስኪዘንብ ድረስ በድንጋይ ላይ ዘረጋችው በቀንም ወፎች በሌሊትም አራዊት ያርፉባቸው ዘንድ አልተወችም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 21:10
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር የተረገመ ስለ ሆነ አስከሬኑ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ አይደር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በርስትነት የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ አስከሬኑን በዚያኑ ዕለት ቅበረው።


እግዚአብሔር በበልግ ወራት ዝናብ እንዲሰጣችሁ ለምኑት፤ ዝናብ ያዘለ ደመናን የሚልክ እግዚአብሔር ነው፤ ዝናብንና የመስክ አትክልትን ለሁሉም የሚሰጥ እርሱ ነው።


“እናንተ የጽዮን ሕዝብ ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ሐሤትም አድርጉ፤ እርሱ በትክክል ፈርዶ እንደ ወትሮው በበጋና በክረምት ወራት በቂ ዝናብ ሰጥቶአችኋል።


ኤልያስ ንግግሩን ከፈጸመ በኋላ አክዓብ ልብሱን በመቅደድና አውልቆ በመጣል ማቅ ለበሰ፤ እህል መቅመስንም እምቢ አለ፤ ማቁንም እንደ ለበሰ ይተኛ ነበር፤ ሲሄድም ከጭንቀቱ ብዛት የተነሣ ፊቱ ጠቊሮ ይታይ ነበር።


ሳኦል የአያ ልጅ የሆነች ሪጽፋ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ ኢያቡስቴ አበኔርን “ለምን ከአባቴ ቁባት ጋር ተገናኘህ” አለው።


የግጦሽ ሣር በማጣት ከብቶች ያላዝናሉ፤ የበጎች መንጋ ሳይቀሩ ተርበው በብርቱ ሥቃይ ላይ ይገኛሉ።


ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።”


ጎግና ሠራዊቱ፥ እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተሰለፉ የጦር ጓደኞቹ ሁሉ ሞተው በእስራኤል ተራራዎች ላይ ይወድቃሉ፤ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ እንዲሆን አደርገዋለሁ።


ከአሕዛብ አማልክት መካከል አንዱ እንኳ ዝናብ ማዝነብ አይችልም፤ ሰማይም በራሱ ፈቃድ ካፊያ አያወርድም፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ስለ ሆንክ እኛ ተስፋ የምናደርገው በአንተ ነው።


ልብስዋን ትለውጥ፤ እርስዋም ከአንተ ጋር በቤትህ ተቀምጣ እስከ አንድ ወር ድረስ በጦርነት ስለሞቱት ወላጆችዋ ታልቅስ፤ ከዚያም በኋላ ሚስት አድርገህ ታገባታለህ።


ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር የክረምቱንና የበልጉን ዝናብ በወቅቱ ለምድራችሁ ይልካል፤ በዚህም ዐይነት ለእናንተ ሲሳይ የሚሆነው እህል፥ ወይን ጠጅና የወይራ ዘይት፥


ቀጥሎም “ወዲህ ና! ሥጋህን ለሰማይ አሞራዎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ” አለው።


በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ ፈርዖን ከዚህ እስር ቤት አውጥቶ ራስህን ካስቈረጠ በኋላ በእንጨት ላይ ያሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”


በዚህች ቀን እግዚአብሔር በአንተ ላይ ድልን ያጐናጽፈኛል፤ እኔም ራስህን እቈርጣለሁ፤ የፍልስጥኤማውያንንም ወታደሮች ሥጋ ለአሞራዎችና ለአራዊት ምግብ አድርጌ እሰጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ መላው ዓለም በእስራኤል ዘንድ አምላክ እንዳለ ያውቃል።


ዳዊት፥ የሳኦል ቁባት የነበረችው ሪጽፋ ያደረገችውን በሰማ ጊዜ፥


“አንድ ሰው በሠራው ከባድ ወንጀል ምክንያት በእንጨት በስቅላት ቢቀጣ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች