ይሁዳ መቃቢስ በበኩሉ ጦር ሠራዊቱን በክፍል በክፍል አሰልፎ፥ ለየክፍሉም አለቃ ሾሞ መቶ ሃያ ሺህ እግረኛ እና ሁለት ሺህ አምስት መቶ ፈረሰኞች አሰልፎ የነበረውን ጢሞቴዎስን ለመውጋት ገሠገሠ።