2 ነገሥት 19:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእኔ ላይ በቍጣ ስለ ተነሣሣህ፣ እብሪትህም ወደ ጆሮዬ ስለ ደረሰ፣ ስናጋዬን በአፍንጫህ አደርጋለሁ፤ ልጓሜን በአፍህ አስገባለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስ አደርግሃለሁ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍጣህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአልና ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ፥ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበት መንገድም እመልስሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍጣህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአልና ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ፥ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ። |
እነሆ፥ እኔ የሽብር ወሬ የሚያሰማ መንፈስ እልክበታለሁ፤ ስለዚህም ወደ አገሩ ተመልሶ እንዲሄድና እዚያም በገዛ ምድሩ በሰይፍ ተመትቶ እንዲሞት አደርጋለሁ።’”
እስትንፋሱም አሕዛብን በአጥፊ ወንፊት ሊነፋቸው እንደሚያጥለቀልቅ እስከ አንገትም እንደሚደርስ ወንዝ ነው፤ በሕዝብም መንጋጋ የሚያስት ልጓም ይሆናል።
በመንጠቆዎችም አድርገው በቀፎ ውስጥ አኖሩት፥ ወደ ባቢሎንም ንጉሥ አመጡት፤ ድምፁ በእስራኤል ተራሮች ላይ ዳግመኛ እንዳይሰማ ወደ እስር ቤት አመጡት።
በመንጋጋህ መንጠቆ አስገባለሁ፥ የወንዞችህን ዓሦች ከቅርፊትህ ጋር አጣብቃለሁ፤ በቅርፊትህ ከተጣበቁት የወንዞችህ ዓሦች ሁሉ ጋር ከወንዞችህ መካከል አወጣሃለሁ።
ወደ ኋላ እመልስሃለሁ፥ መንጠቆ በመንጋጋህ አስገባሃለሁ፥ አንተንና ሠራዊትህን ሁሉ፥ ፈረሶችን፥ ፈረሰኞችን፥ የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ሁሉም ሰይፍ የያዙ ጋሻና ራስ ቁርን ካደረጉ ታላቅ ጉባኤ ጋር አወጣሃለሁ፥
“እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፤ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።