Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 19:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ቍጣ​ህና ትዕ​ቢ​ትህ ወደ ጆሮዬ ደር​ሶ​አ​ልና ስለ​ዚህ ስና​ጋ​ዬን በአ​ፍ​ን​ጫህ፥ ልጓ​ሜ​ንም በከ​ን​ፈ​ርህ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በመ​ጣ​ህ​በት መን​ገ​ድም እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በእኔ ላይ በቍጣ ስለ ተነሣሣህ፣ እብሪትህም ወደ ጆሮዬ ስለ ደረሰ፣ ስናጋዬን በአፍንጫህ አደርጋለሁ፤ ልጓሜን በአፍህ አስገባለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እንድትመለስ አደርግሃለሁ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ስናጋ፥ በአፍህ ልጓም አድርጌ፥ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ቍጣህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአልና ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ፥ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 19:28
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ጣ​በት መን​ገድ በዚያ ይመ​ለ​ሳል እንጂ፥ ወደ​ዚ​ህ​ችም ከተማ አይ​ገ​ባም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እነሆ፥ በላዩ መን​ፈ​ስን እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ወሬ​ንም ይሰ​ማል፤ ወደ ምድ​ሩም ይመ​ለ​ሳል፤ በም​ድ​ሩም በሰ​ይፍ እን​ዲ​ወ​ድቅ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ በሉት።”


በአ​ን​ገቱ ኀይል ታድ​ራ​ለች፤ ለሚ​ያ​የ​ውም በፊቱ ሞት ይው​ላል።


የሚ​ከ​ራ​ከ​ረ​ኝና በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ርስ ማን ነው? ከሰ​ማይ በታች ያለ​ውም ሁሉ የእኔ ነው።


እርሱ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና፥ ሆኑ፤ እርሱ አዘዘ፤ ተፈ​ጠ​ሩም።


ዘምሩ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለን​ጉ​ሣ​ችን ዘምሩ።


በኀ​ይሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዛል፤ ዐይ​ኖቹ ወደ አሕ​ዛብ ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ የም​ታ​ውቁ ራሳ​ች​ሁን ከፍ ከፍ አታ​ድ​ርጉ።


አቤቱ፥ በመ​ዓ​ትህ ተነሥ፤ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ተነ​ሣ​ባ​ቸው፤ አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ባዘ​ዝ​ኸው ሥር​ዐት ተነሥ።


ኃጥ​ኣ​ንን አል​ኋ​ቸው፥ “አት​በ​ድሉ” የሚ​በ​ድ​ሉ​ት​ንም አል​ኋ​ቸው፥ “ቀን​ዳ​ች​ሁን አታ​ንሡ፥


አቤቱ፥ ነፍሴ አደ​ባ​ባ​ዮ​ች​ህን በመ​ው​ደድ ደስ አላት፤ ልቤም ሥጋ​ዬም በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አላ​ቸው።


እስ​ት​ን​ፋ​ሱም አሕ​ዛ​ብን ስለ ከንቱ ስሕ​ተ​ታ​ቸው ሊከ​ፋ​ፍ​ላ​ቸው በሸ​ለቆ እን​ደ​ሚ​ያ​ጥ​ለ​ቀ​ልቅ፥ እስከ አን​ገ​ትም እን​ደ​ሚ​ደ​ር​ስና እን​ደ​ሚ​ከ​ፋ​ፍል ውኃ ይጐ​ር​ፋል፤ ስሕ​ተ​ታ​ቸ​ውም ይከ​ተ​ላ​ቸ​ዋል፤ ይወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋ​ልም።


በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስ​ረው በቀፎ ውስጥ አኖ​ሩት፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አመ​ጡት፤ ድም​ፁም በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ ከዚያ ወዲያ እን​ዳ​ይ​ሰማ ወደ ግዞት ቤት አገ​ቡት።


በመ​ን​ጋ​ጋ​ዎ​ችህ መቃ​ጥን አገ​ባ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የወ​ን​ዞ​ች​ህ​ንም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅር​ፊ​ትህ አጣ​ብ​ቃ​ለሁ፤ ከወ​ን​ዞ​ች​ህም መካ​ከል አወ​ጣ​ሃ​ለሁ፤ የወ​ን​ዞ​ች​ህም ዓሦች ሁሉ ወደ ቅር​ፊ​ትህ ይጣ​በ​ቃሉ።


አንተ አፍ​ህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደ​ረ​ግህ እኔ ሰም​ቼ​አ​ለሁ።”


እመ​ል​ስ​ህ​ማ​ለሁ፤ በመ​ን​ጋ​ጋ​ህም ልጓም አገ​ባ​ብ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተ​ንና ሠራ​ዊ​ት​ህን ሁሉ፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን፥ የጦር ልብስ የለ​በ​ሱ​ትን ሁሉ፥ ጋሻና ራስ ቍርን፥ ሰይ​ፍ​ንም የያ​ዙ​ትን ሁሉ አወ​ጣ​ለሁ።


ጌታ አግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “እና​ን​ተን በሰ​ልፍ ዕቃ፥ ቅሬ​ታ​ች​ሁ​ንም በመ​ቃ​ጥን የሚ​ወ​ስ​ዱ​በት ቀን እነሆ በላ​ያ​ችሁ ይመ​ጣል” ብሎ በቅ​ዱ​ስ​ነቱ ምሎ​አል።


እነ​ርሱ ግን፥ እጅግ ተቈጡ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱ​ስም ምን እን​ድ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​በት እርስ በር​ሳ​ቸው ተማ​ከሩ።


“ዓለም ቢጠ​ላ​ችሁ አስ​ቀ​ድሞ እኔን እንደ ጠላ ዕወቁ።


“እና​ንተ አን​ገ​ታ​ችሁ የደ​ነ​ደነ፥ ልባ​ች​ሁም የተ​ደ​ፈነ፥ ጆሮ​አ​ች​ሁም የደ​ነ​ቈረ፥ እንደ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ዘወ​ትር ትቃ​ወ​ማ​ላ​ችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች