አሁንም እመክርሃለሁና ቃሌን ስማ፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቡን አቅርብ፥ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አቅርብ፤
2 ቆሮንቶስ 3:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክርስቶስም በኩል በእግዚአብሔር ያለን መተማመን ይህን ይመስላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት ይህን የመሰለ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን የምንልበት ምክንያት በክርስቶስ አማካይነት በእግዚአብሔር ላይ እምነት ስላለን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ ያለ እምነት አለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክርስቶስም በኩል ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ያለ እምነት አለን። |
አሁንም እመክርሃለሁና ቃሌን ስማ፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቡን አቅርብ፥ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አቅርብ፤
ከእናንተ በመቄዶንያና በአካያ የጌታ ቃል ብቻ አልነበረም የተሰማው፥ ነገር ግን በሁሉ ስፍራ የተወራው በእግዚአብሔር ያላችሁ እምነትም ጭምር ነበር እንጂ፤ ስለዚህም እኛ ምንም መናገር አያስፈልገንም።