1 ተሰሎንቄ 1:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ከእናንተ በመቄዶንያና በአካያ የጌታ ቃል ብቻ አልነበረም የተሰማው፥ ነገር ግን በሁሉ ስፍራ የተወራው በእግዚአብሔር ያላችሁ እምነትም ጭምር ነበር እንጂ፤ ስለዚህም እኛ ምንም መናገር አያስፈልገንም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 የጌታ ቃል ከእናንተ ወጥቶ በመቄዶንያና በአካይያ መሰማቱ ብቻ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ያላችሁ እምነት በሁሉ ቦታ ታውቋል፤ ስለዚህ እኛ በዚህ ጕዳይ ላይ ምንም መናገር አያስፈልገንም፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 የጌታ ቃል ከእናንተ ወጥቶ የተሰማው በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ያላችሁ እምነት በሁሉ ቦታ ታውቆ ነበር፤ በዚህ ምክንያት እኛ ስለዚህ ጉዳይ ምንም መናገር አያስፈልገንም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ከእናንተ ወጥቶ የጌታ ቃል በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አልተሰማምና፤ ነገር ግን ምንም እንድንናገር እስከማያስፈልግ ድረስ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቶአል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ከእናንተ ወጥቶ የጌታ ቃል በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አልተሰማምና፥ ነገር ግን ምንም እንድንናገር እስከማያስፈልግ ድረስ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቶአል። ምዕራፉን ተመልከት |