ዘፀአት 18:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 አሁንም እመክርሃለሁና ቃሌን ስማ፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቡን አቅርብ፥ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አቅርብ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ምክር እሰጥሃለሁና አሁን እኔን ስሙኝ፤ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ይሁን። አንተ በእግዚአብሔር ፊት ሕዝብን የምትወክል መሆን አለብህ፤ ክርክራቸውን ወደ እርሱ ታቀርባለህ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 እነሆ፥ እኔ አንድ ነገር ልምከርህ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አንተ ሕዝቡን ወክለህ በእግዚአብሔር ፊት ጉዳያቸውን አቅርብ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 አሁንም እመክርሃለሁና ስማኝ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ለሕዝቡ ሁን፤ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አድርስ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 አሁንም እመክርሃለሁና ቃሌን ስማ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ለሕዝቡ ሁን፥ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አድርስ፤ ምዕራፉን ተመልከት |