2 ቆሮንቶስ 11:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትምክህት የሚያስፈልግ ከሆነ፥ መድከሜን በሚያሳይ ነገር እመካለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መመካት ካለብኝ፣ ደካማነቴን በሚያሳዩ ነገሮች እመካለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መመካት የሚያስፈልግ ቢሆን እኔ የምመካው ደካማነቴን በሚያሳዩ ነገሮች ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መመካት የሚገባ ከሆነስ እኔም በመከራዬ እመካለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትምክህት የሚያስፈልግ ከሆነ፥ ከድካሜ በሚሆነው ነገር እመካለሁ። |
ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትን ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝቡ መካከል ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዘዋወር ነበር።
አሁን በመከራዬ ስለ እናንተ ደስ ይለኛል፤ አካሉም ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ ካለፈባቸው መከራዎች መካከል የጐደሉትን በሥጋዬ እፈጽማለሁ።