Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እኔም በድካምና በፍርሃት በብዙ መንቀጥቀጥም በእናንተ ዘንድ ነበርሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ወደ እናንተ የመጣሁት በድካምና በፍርሀት፣ እንዲሁም በብዙ መንቀጥቀጥ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለዚህ ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ደካማ ሆኜ በፍርሃትና በብዙ መንቀጥቀጥ ላይ ነበርኩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እኔም በድ​ካ​ምና በፍ​ር​ሀት፥ በብዙ መን​ቀ​ጥ​ቀ​ጥም መጣሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እኔም በድካምና በፍርሃት በብዙ መንቀጥቀጥም በእናንተ ዘንድ ነበርሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 2:3
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በድካም ተሰቅሎአል፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል በሕይወት ይኖራል። እኛ ደግሞ ከእርሱ ጋር ደካሞች ብንሆን፤ እናንተ ለማገልገል በእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋር በሕይወት እንኖራለን።


እኛ ስንደክም እናንተም ኀይለኞች ስትበረቱ ደስ ብሎናልና፥ ፍጹማን እንድትሆኑ ደግሞ እንጸልያለን።


አንዳንዶች “መልእክቶቹ ከባድና ጠንካራ ናቸው፤ ሰውነቱ ሲታይ ግን ደካማ ነው፤ ንግግሩም የተናቀ ነው፤” ይላሉ።


እኔም ጳውሎስ፥ ፊት ለፊት ሳገኛችሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ርቄ ግን ደፋር የምሆንባችሁ፥ በክርስቶስ የዋህነትና ገርነት እመክራችኋለሁ፤


ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች በሁሉም መንገድ ራሳችንን እንሰጣለን፤ በታላቅ ጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥


ስለዚህ አንታክትም፤ ውጫዊው ሰውነታችን እየመነመነ ቢሄድ እንኳን፥ ውስጣዊው ሰውነታችን በየዕለቱ ይታደሳል።


ስለዚህ ይህ አገልግሎት የተሰጠን በእግዚአብሔር ምሕረት ምክንያት ስለሆነ፥ መቼም አንታክትም።


ጋልዮስም በአካይያ አገረ ገዥ በነበረ ጊዜ፥ አይሁድ በአንድ ልብ ሆነው በጳውሎስ ላይ ተነሡ፤ ወደ ፍርድ ወንበርም አምጥተው


ነገር ግን በተቃወሙትና በተሳደቡ ጊዜ፥ ልብሱን እያራገፈ “ደማችሁ በራሳችሁ ነው፤ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ፤” አላቸው።


ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አልነበረውም፤ ከውጭ ጠብ ነበረ፤ ከውስጥ ደግሞ ፍርሃት ነበረብን።


በአንፊጶሊስና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፤ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።


ከዚህም በኋላ ጳውሎስ ከአቴና ወጥቶ ወደ ቆሮንቶስ መጣ።


በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፥ የሠራዊት ጌታም በእነርሱ ላይ ከሚያንቀሳቅሳት ከእጁ የተነሣ ይርዳሉ ይፈራሉም።


ስለዚህም በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደ ተቀበላችሁት፥ የሁላችሁን መታዘዝ እያሰበ ለእናንተ ያለው ፍቅር እጅግ ጨምሯል።


አገልጋዮች ሆይ! ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ፥ በልባችሁ ቅንነት በምድር ጌቶቻችሁ ለሆኑ ታዘዙ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች