1 ሳሙኤል 7:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የጌታን ታቦት ይዘው ወጡ፤ ከዚያም በኮረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት ወሰዱት። የጌታን ታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቂርያትይዓይሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ወጡ፤ ከዚያም በኰረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት ወሰዱት። የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲጠብቅም ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቂርያትይዓሪም ሰዎችም የእግዚአብሔርን ታቦት ወስደው በኮረብታ ላይ ወደሚኖረው አቢናዳብ ተብሎ ወደሚጠራ ሰው ቤት አስገቡት፤ የእግዚአብሔርንም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን የተለየ እንዲሆን አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አወጡ፤ በኮረብታውም ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አገቡአት፤ የእግዚአብሔርንም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት አወጡ፥ በኮረብታውም ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አገቡት፥ የእግዚአብሔርንም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት። |
ድንበሩም ወደ ምዕራብ ሄደ፥ በቤትሖሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ ደቡብ ዞረ፤ መጨረሻውም ቂርያት-ይዓሪም በምትባል በቂርያትበኣል በይሁዳ ልጆች ከተማ ነበረ፤ ይህ የምዕራቡ ዳርቻ ነበረ።
ከዚያም ወደ ቂርያትይዓሪም ሰዎች መልእክተኞች ልከው፥ “ፍልስጥኤማውያን የጌታን ታቦት መልሰውልናል፤ መጥታችሁ ወደ እናንተ ውሰዱት” አሏቸው።