Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ዜና መዋዕል 13:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በሳኦልም ዘመን አልፈለግነውምና የአምላካችንን ታቦት ወደ እኛ እንመልስ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በሳኦል ዘመነ መንግሥት ሳንፈልገው የነበረውን የአምላካችንን ታቦት መልሰን ወደ እኛ እናምጣ”።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በሳኦል ዘመነ መንግሥት ችላ ብለነው የነበረውንም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሄደን እናመጣለን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከሳ​ኦ​ልም ዘመን ጀምሮ አል​ፈ​ለ​ጓ​ት​ምና የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ወደ እኛ እን​መ​ል​ሳት” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በሳኦልም ዘመን አልፈለግነውምና የአምላካችንን ታቦት ወደ እኛ እንመልስ፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዜና መዋዕል 13:3
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊትም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “መልካም መስሎ ቢታያችሁ፥ የጌታም የአምላካችን ፈቃድ ቢሆን፥ በእስራኤል አገር ሁሉ ለቀሩት ወንድሞቻችን በከተሞቻቸውና በመሰማሪያዎቻቸውም ለተቀመጡት ካህናትና ሌዋውያን ወደ እኛ እንዲሰበሰቡ እንላክባቸው፤


ነገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዐይን ዘንድ ቅን ነበረና ጉባኤው ሁሉ፦ “እንዲሁ እናደርጋለን” አሉ።


ቀድሞም አልተሸከማችሁትምና፥ እንደ ሥርዓቱም አልፈለግነውምና ጌታ አምላካችን በመካከላችን ቊጣውን አወረደ።”


እነሆ፥ በኤፍራታ ሰማነው፥ በጁኦሪም ምድር አገኘነው።


ሳኦልም አኪያን፥ “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደዚህ አምጣ” አለው፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ታቦት በእስራኤላውያን ዘንድ ነበር።


ከዚያም በኋላ ሳኦልም፥ “ፍልስጥኤማውያንን ተከትለን በሌሊት እንውረድና እስኪ ነጋ ድረስ እንዝረፋቸው፤ አንድም ሰው በሕይወት አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ” ብለው መለሱለት። ካህኑ ግን፥ “ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ” አለ።


ዳዊትም ምን ማድረግ እንደሚገባው አቢሜሌክ ጌታን ጠይቆለታል፤ ለዳዊትም ጥቂት ምግብና የፍልስጥኤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጥቶታል” ሲል ተናገረ።


ስለ እርሱ እግዚአብሔርን ስጠይቅስ ያ ቀን የመጀመሪያ ጊዜዬ ነበርን? ፈጽሞ አልነበረም፤ ይህን ጉዳይ በተመለከተ አገልጋይህ የሚያውቀው ምንም ነገር ስለ ሌለ ንጉሥ እኔን አገልጋዩን ወይም ከአባቴ ቤተሰብ ማንንም ጥፋተኛ አያድርግ።”


እርሱም፥ “እነዚህን ፍልስኤማውያን ሄጄ ልምታን?” ሲል ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “ሂድ፤ ፍልስጥኤማውያንን ምታ፤ ቅዒላንም አድናት” ብሎ መለሰለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች