1 ሳሙኤል 14:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል፥ “ዛሬ ጠላቶቼን ከመበቀሌ በፊት፥ እስከ ማታ ድረስ እህል የሚበላ ሰው የተረገመ ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አስምሎ ስለ ነበር፥ በዚያች ዕለት የእስራኤል ሰዎች ተጨንቀው ዋሉ፤ ስለዚህ ከሕዝቡ አንድም እህል የቀመሰ አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል፣ “ዛሬ ጠላቶቼን ከመበቀሌ በፊት እስከ ማታ ድረስ እህል የሚበላ ሰው የተረገመ ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አምሎ ስለ ነበር፣ በዚያች ዕለት የእስራኤል ሰዎች ተጨንቀው ዋሉ፤ ስለዚህ ከሕዝቡ አንድም እህል የቀመሰ አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን እስራኤላውያን በራብ ደከሙ፤ ምክንያቱም ሳኦል “ጠላቶቼን እስክበቀል ድረስ ዛሬ እህል ውሃ የሚቀምስ ማናቸውም ሰው የተረገመ ይሁን!” ብሎ ሕዝቡን በማስማል ማንም ሰው እህል ውሃ እንዳይቀምስ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር። ከዚህም የተነሣ ሁሉም ምንም ነገር ሳይቀምሱ ቀኑን ሙሉ ዋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም በዚያ ቀን ትልቅ በደል ፈጸመ፤ “ጠላቶቼን እስክበቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን” ብሎ ሕዝቡን አምሎአቸው ነበርና። ሕዝቡም ሁሉ እህል አልቀመሱም። ሀገሩም ሁሉ ምሳ አልበላም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ሰዎች በዚያ ቀን ተጨነቁ፥ ሳኦል፦ ጠላቶቼን እስክበቀል እስከ ማታ ድረስ መብል የሚበላ ሰው ርጉም ይሁን ብሎ ሕዝቡን አምሎአቸው ነበርና። ሕዝቡም ሁሉ መብል አልቀመሱም። |
ማናቸውም ሰው ክፉን ወይም መልካምን ለማድረግ ሳያስብ በከንፈሩ ተናግሮ ቢምል፤ ሳያስብ የማለው ስለ ማናቸውም ነገር ቢሆን፤ ይህንንም ሳይታወቀው ቢያደርግ፤ በታወቀው ጊዜ ከዚህ ነገር በአንዱ በደለኛ ይሆናል።
ካህኑም ሴቲቱን በመርገም መሐላ ያምላታል፥ ካህኑም ሴቲቱን እንዲህ ይላታል፦ ‘ጌታ ጭንሽን እያመነመነ ሆድሽንም እየነፋ፥ በሕዝብሽ መካከል ጌታ ለመርገምና ለመሐላ የምትሆኚ ያድርግሽ፤
በዚያን ጊዜም ኢያሱ እንዲህ ብሎ ማለ፦ “ይህችን ከተማ ኢያሪኮን ለመሥራት የሚነሣ ሰው በጌታ ፊት ርጉም ይሁን፤ መሠረትዋን ሲጀምር በኩር ልጁ ይጥፋ፥ በርዋንም ሲያቆም ታናሹ ልጁ ይጥፋ።”
እስራኤልን የታደገ ሕያው ጌታን! አድራጊው ልጄ ዮናታን እንኳ ቢሆን መሞት አለበት።” ነገር ግን ከሕዝቡ መካከል የመለሰለት አንድም አልነበረም።
ሳኦልም፥ “ዳዊትን፥ ‘ንጉሡም ለልጅቱ ካንተ የሚፈልገው ጥሎሽ ጠላቶቹን ለመበቀል የመቶ ፍልስጥኤማውያንን ሸለፈት እንጂ ሌላ አይደለም ብላችሁ ንገሩት’ ” አላቸው። ሳኦል ይህን ያቀደው ዳዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲወድቅ ነበር።