Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 16:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ! ና!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታ ሆይ፤ ና!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን! ጌታችን ሆይ፥ ና!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ጌታ​ች​ንን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን የማ​ይ​ወ​ደው የተ​ለየ ይሁን፤ ጌታ​ችን ይመ​ጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ፥ ና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 16:22
32 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ከሚወዱ ሁሉ ጋር ጸጋ ይሁን፤ አሜን።


ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”


ኢየሱስ መሢሕ መሆኑን የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።


እርሱ አስቀድሞ ስለወደደን፥ እንወዳለን።


ኢየሱስም አላቸው “እግዚአብሔርስ አባታችሁ ቢሆን ኖሮ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና።


ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔም ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።


ይህን የሚመሰክር “አዎን በቶሎ እመጣለሁ፤” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።


እንግዲህ ለእናንተ ለምታምኑት ይህ ድንጋይ ክቡር ነው፤ ለማያምኑት ግን “ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ።”


እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩትም በእርሱ በማመናችሁ መግለጽ በማይቻልና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ብሎአችኋል።


እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።


ስለ ሥጋ ዘመዶቼና ስለ ወንድሞቼ ስል እኔ ራሴ ከክርስቶስ ተለይቼ የተረገምሁ እንድሆን እመኝ ነበር።


በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ በክርስቶስ ኢየሱስ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አይጠቅምም።


ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር “ኢየሱስ የተረገመ ነው፤” የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው፤” ሊል ማንም እንደማይችል አስታውቃችኋለሁ።


እነርሱም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ሽማግሌዎቹ መጥተው “ጳውሎስን እስክንገድል ድረስ ምንም እንዳንቀምስ ተረጋግመን ተማምለናል።


እርሱ ያከብረኛል፤ የእኔ ከሆነው ወስዶ ይነግራችኋልና።


ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተዋል፤ ጠልተውማል።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን፤ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።


“የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።


ደግሞም ስለ ወይን ቦታው ልዘምር፤ ስለ ወዳጄ፤ ወዳጄ በለምለም ኮረብታ ላይ


አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፥ እርሱም ፈጽሞ ያማረ ነው፥ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ባልንጀራዬም ይህ ነው።


ነፍሴ የወደደችህ አንተ ንገረኝ፥ ወዴት ታሰማራለህ? በቀትርስ ጊዜ ወዴት ትመስጋለህ? ስለ ምንስ ከባልንጀሮችህ መንጎች በኋላ እቅበዘበዛለሁ?


ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ። ጌታ መምጫው ቀርቦአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች