ይሁዳ በገለዓድ የተገኙትን እስራኤላውያንን ትልቁንም ትንሹንም በሙሉ ከነሚስቶቻቸው፤ ከነልጆቻቸው፤ ከነንብረቶቻቸው በአንድነት ሰበሰባቸው፤ በጣም ብዙ ሕዝብ ነበረ፤ ሁሉም ወደ ይሁዳ አገር እንዲሄዱ ተደረገ።