ከዚህ በኋላ የሰርጉ በዐል ባለቀ ጊዜ ጦብያ ራጉኤልን አለው፥ “እንግዲህስ ወዲያ አሰናብተኝ፤ አባቴና እናቴ ተስፋ ቈርጠዋልና እንግዲህ ወዲህም ያዩኝ ዘንድ ተስፋ አያደርጉምና፥”
ራጉኤልም ጦብያን “ቆይ ልጄ ከእኔ ጋር ቆይ፥ ወደ አባትህ ወደ ጦቢት ያንተን ሁኔታ እንዲነግሩት መልዕክተኞችን እልካለሁ” አለው።