የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 127:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የድ​ካ​ም​ህን ፍሬ ትመ​ገ​ባ​ለህ፤ ብፁዕ ነህ፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ል​ሃል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የዕለት ጕርስ ለማግኘት በመጣር፣ ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤ እርሱ ለሚወድዳቸው እንቅልፍን ያድላልና።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥ ማለዳ መነሣታችሁ፥ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው። እርሱ ለሚወዱት እንቅልፍን ይሰጣልና።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በማለዳ እየተነሡና በምሽትም እየዘገዩ ለኑሮ መድከም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሰዎች ገና ተኝተው ሳሉ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ያዘጋጅላቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 127:2
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ተስ​ፋ​ህ​ንም ታገኝ ዘንድ ተዘ​ል​ለህ ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ ያለ ኀዘ​ንና ጭን​ቀ​ትም በደ​ኅ​ን​ነት ትኖ​ራ​ለህ።


እኔ ተኛሁ፤ አን​ቀ​ላ​ፋ​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ሥ​ቶ​ኛ​ልና ተነ​ሣሁ።


በእ​ርሱ በሰ​ላም እተ​ኛ​ለሁ፥ አን​ቀ​ላ​ፋ​ለ​ሁም፤ አቤቱ፥አንተ ብቻ​ህን በተ​ስፋ አሳ​ድ​ረ​ኸ​ኛ​ልና።


አም​ላኬ፥ አንተ ጸሎ​ቴን ሰም​ተ​ሃ​ልና፤ ለሚ​ፈ​ሩ​ህም ርስ​ትን ሰጠ​ሃ​ቸው።


የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ሆና ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ወደ ልብ አታመጣም።


ከፀ​ሐይ በታች የተ​ሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


አንድ ሰው ብቻ​ውን አለ፥ ሁለ​ተ​ኛም የለ​ውም፥ ልጅም ሆነ ወን​ድም የለ​ውም፤ ለድ​ካሙ ግን መጨ​ረሻ የለ​ውም፥ ዐይ​ኖ​ቹም ከባ​ለ​ጠ​ግ​ነት አይ​ጠ​ግ​ቡም። ለማን እደ​ክ​ማ​ለሁ? ሰው​ነ​ቴ​ንስ ከደ​ስታ ለምን እነ​ፍ​ጋ​ታ​ለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።


ብዙ ወይም ጥቂት ቢበላ የአ​ገ​ል​ጋይ እን​ቅ​ልፉ ጣፋጭ ነው፤ ብል​ጽ​ግ​ናን ያበዛ ሰውን ግን ይተኛ ዘንድ የሚ​ተ​ወው የለም።


የሰው ድካም ሁሉ በአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አት​ጠ​ግ​ብም።


ስለ​ዚህ ነቃሁ፤ ተመ​ለ​ከ​ት​ሁም፤ እን​ቅ​ል​ፌም ጣፈ​ጠኝ።


“የሰ​ላ​ም​ንም ቃል ኪዳን ከዳ​ዊት ቤት ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ክፉ​ዎ​ች​ንም አራ​ዊት ከም​ድር አጠ​ፋ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ውም በም​ድረ በዳ ይኖ​ራሉ፤ በዱ​ርም ውስጥ ይተ​ኛሉ።