Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መክብብ 1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ሁሉ ነገር ከንቱ ስለ መሆኑ

1 በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለእ​ስ​ራ​ኤል የነ​ገሠ የዳ​ዊት ልጅ የሰ​ባ​ኪው የሰ​ሎ​ሞን ቃል።

2 ሰባ​ኪው፥ “ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከ​ንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው” ይላል።

3 ከፀ​ሐይ በታች በሚ​ደ​ክ​ም​በት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምን​ድን ነው?

4 ትው​ልድ ያል​ፋል፥ ትው​ል​ድም ይመ​ጣል፤ ምድር ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጸንታ ትኖ​ራ​ለች።

5 ፀሐይ ይወ​ጣል፥ ፀሐ​ይም ይገ​ባል፥ ወደ​ሚ​ወ​ጣ​በ​ትም ስፍራ ይመ​ለ​ሳል፤

6 ወደ ቀኝ ይመ​ለ​ሳል፥ ወደ ሰሜ​ንም ይዞ​ራል፤ ነፋስ ዙሪ​ያ​ዉን ዙሮ ይሄ​ዳል፥ ነፋ​ስም በዙ​ረቱ ይመ​ለ​ሳል።

7 ፈሳ​ሾች ሁሉ ወደ ባሕር ይሄ​ዳሉ፥ ባሕሩ ግን አይ​ሞ​ላም፤ ፈሳ​ሾች ወደ​ሚ​ሄ​ዱ​በት ስፍራ እንደ ገና ወደ​ዚያ ይመ​ለ​ሳሉ።

8 ነገር ሁሉ ያደ​ክ​ማል፤ ሰውም ይና​ገ​ረው ዘንድ አይ​ች​ልም፥ ዐይን በማ​የት አይ​ጠ​ግ​ብም፥ ጆሮም በመ​ስ​ማት አይ​ሞ​ላም።

9 የሆ​ነው ነገር እርሱ የሚ​ሆን ነው፥ የተ​ደ​ረ​ገ​ውም ነገር እርሱ የሚ​ደ​ረግ ነው፥ ከፀ​ሐ​ይም በታች ከተ​ደ​ረ​ገው ሁሉ አዲስ ነገር የለም።

10 እነሆ፥ “ይህ ነገር አዲስ ነው” ብሎ የሚ​ና​ገር ማን ነው? እርሱ ከእኛ በፊት በነ​በ​ሩት ዘመ​ናት ተደ​ር​ጓል።

11 ለፊ​ተ​ኞቹ ነገ​ሮች መታ​ሰ​ቢያ የላ​ቸ​ውም፤ ለኋ​ለ​ኞ​ቹም ነገ​ሮች ከእ​ነ​ርሱ በኋላ በሚ​ነ​ሡት ሰዎች ዘንድ መታ​ሰ​ቢያ አይ​ገ​ኝ​ላ​ቸ​ውም።

12 እኔ ሰባ​ኪው በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ ነበ​ርሁ።

13 ከሰ​ማ​ይም በታች ስለ​ተ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በጥ​በብ ለመ​መ​ር​መ​ርና ለመ​ፈ​ተን ልቤን አተ​ጋሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይደ​ክ​ሙ​በት ዘንድ ክፉ ድካ​ምን ለሰው ልጆች ሰጥ​ት​ዋ​ልና።

14 ከፀ​ሐይ በታች የተ​ሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።

15 ጠማማ ይቀና ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ጐደ​ሎም ይቈ​ጠር ዘን​ድ​አ​ይ​ች​ልም።

16 እኔ በልቤ፥ “እነሆ፥ ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ጥበ​ብን አበ​ዛሁ፤ ልቤ​ንም ለጥ​በ​ብና ለዕ​ው​ቀት ሰጠሁ፥” በማ​ለት ተና​ገ​ርሁ።

17 ልቤም ብዙ ጥበ​ብ​ንና አእ​ም​ሮን፥ ምሳ​ሌ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን ተመ​ለ​ከ​ተች። ይህም ነፋ​ስን መከ​ተል እንደ ሆነ አስ​ተ​ዋ​ልሁ።

18 በጥ​በብ መብ​ዛት ትካዜ ይበ​ዛ​ልና፤ ዕው​ቀ​ት​ንም የሚ​ያ​በዛ መከ​ራን ያበ​ዛ​ልና።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች