Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መክብብ 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከፀ​ሐይ በታች በሚ​ደ​ክ​ም​በት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምን​ድን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከፀሓይ በታች ከሚለፋበት ተግባር ሁሉ፣ ሰው ምን ትርፍ ያገኛል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሰው በሚኖርበት ዓለም በሥራ የሚደክምበት ነገር ሁሉ ትርፉ ምንድን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድር ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መክብብ 1:3
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እጄ የሠ​ራ​ቻ​ትን ሥራ​ዬን ሁሉ፥ የደ​ከ​ም​ሁ​በ​ት​ንም ድካ​ሜን ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነበረ፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም ትርፍ አል​ነ​በ​ረም።


ከእኔ በኋላ ለሚ​ወ​ለድ ሰው እተ​ወ​ዋ​ለ​ሁና ከፀ​ሐይ በታች እኔ የደ​ከ​ም​ሁ​በ​ትን ድካም ሁሉ ጠላ​ሁት።


ጠቢብ ወይም አላ​ዋቂ እን​ደ​ሚ​ሆን ከፀ​ሐይ በታ​ችም በደ​ከ​ም​ሁ​በ​ትና ጠቢብ በሆ​ን​ሁ​በት በድ​ካሜ ሁሉ ይሰ​ለ​ጥን እንደ ሆነ የሚ​ያ​ውቅ ሰው ማን ነው? ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።


ከፀ​ሐይ በታች በደ​ከ​መ​በት ድካ​ምና በልቡ ዐሳብ ሁሉ ለሰው አይ​ሆ​ን​ለ​ት​ምና፤


ለሠ​ራ​ተኛ የድ​ካሙ ትርፍ ምን​ድን ነው?


ከእ​ነ​ዚ​ህም ከሁ​ለቱ ይልቅ ገና ያል​ተ​ወ​ለ​ደው ከፀ​ሓ​ይም በታች የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ክፉ ሥራ ሁሉ ያላየ ይሻ​ላል።


እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ከንቱ ነገ​ርን አየሁ።


ይህም ደግሞ የሚ​ያ​ሳ​ዝን ክፉ ደዌ ነው፥ እንደ መጣ እን​ዲሁ ይሄ​ዳ​ልና፥ ለሰ​ው​ነቱ ለሚ​ደ​ክም ሰው ትርፉ ምን​ድን ነው?


እነሆ፥ እኔ ያየ​ሁት መል​ካ​ምና የተ​ዋበ ነገር፦ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠው በሕ​ይ​ወቱ ዘመን ሁሉ ይበ​ላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም በሚ​ደ​ክ​ም​በት ድካም ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው፤ ይህ ዕድል ፈን​ታው ነውና።


ሰው በከ​ንቱ ወራቱ ቍጥ​ርና እንደ ጥላ በሚ​ያ​ሳ​ል​ፈው ዘመኑ በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ለሰው የሚ​ሻ​ለ​ውን የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው? ወይስ ለሰው ከፀ​ሓይ በታች ከእ​ርሱ በኋላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ማን ይነ​ግ​ረ​ዋል?


ጥበብ ከር​ስት ጋር መል​ካም ነው፤ ፀሓ​ይ​ንም ለሚ​ያዩ ሰዎች ትር​ፍን ይሰ​ጣል።


ከፀ​ሓይ በታ​ችም ጥበ​ብን አየሁ፥ እር​ስ​ዋም በእኔ ዘንድ ታላቅ ናት።


ከፀ​ሓይ በታች የተ​ደ​ረ​ገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግ​ሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋ​ትን ትሞ​ላ​ለች፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ሳሉ ሁከት በል​ባ​ቸው አለ፥ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሙታን ይወ​ር​ዳሉ።


ፍቅ​ራ​ቸ​ውና ጥላ​ቸው ቅን​አ​ታ​ቸ​ውም በአ​ን​ድ​ነት እነሆ፥ ጠፍ​ቶ​አል፤ ከፀ​ሓይ በታ​ችም በሚ​ሠ​ራው ነገር ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዕድል ፈንታ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የላ​ቸ​ውም።


ገን​ዘ​ብን እን​ጀራ ላይ​ደለ፥ የድ​ካ​ማ​ች​ሁ​ንም ዋጋ ለማ​ያ​ጠ​ግብ ነገር ለምን ትመ​ዝ​ና​ላ​ችሁ? አድ​ም​ጡኝ፤ በረ​ከ​ት​ንም ብሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ደስ ይበ​ለው።


እነሆ፥ አሕዛብ ስለ እሳት እንዲሠሩ፥ ወገኖችም ስለ ከንቱነት እንዲደክሙ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ አይደለምን?


የተቀረጸውን ምስል ሠሪው የቀረጸው ለምን ጥቅም ነው? ዲዳንም ጣዖት ይሠራ ዘንድ ሠሪው የታመነበቱ፥ ሐሰትን የሚያስተምር ቀልጦ የተሠራ ምን ይጠቅማል?


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


የሰው ልጅ ለሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ለሚ​ኖር መብል ሥሩ እንጂ ለሚ​ጠ​ፋው መብል አይ​ደ​ለም፤ ይህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ አት​ሞ​ታ​ልና።”


እና​ን​ተም እንደ እነ​ዚህ ላሉ​ትና ከእኛ ጋር በሥራ ተባ​ብሮ ለሚ​ደ​ክም ሁሉ ትታ​ዘ​ዙ​ላ​ቸው ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች