የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ይገ​ዙ​አት ዘንድ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የም​ሰ​ጣ​ትን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር የሚ​ሰ​ልሉ ሰዎ​ችን ላክ፤ ከአ​ባ​ቶች ቤት ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ነገድ ሁሉ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አለቃ የሆነ አንድ አንድ ሰው ትል​ካ​ላ​ችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነዓንን ምድር እንዲሰልሉ ጥቂት ሰዎች ላክ፤ ከእያንዳንዱም የአባቶች ነገድ አለቃ ይላክ።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ለእስራኤል ልጆች የምሰጣትን የከንዓንን ምድር እንዲሰልሉ ሰዎችን ላክ፤ ከአባቶች ነገድ ሁሉ እያንዳንዱ በመካከላቸው አለቃ የሆነ አንድ ሰው ትልካላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አንዳንድ የሕዝብ መሪዎችን መርጠህ፥ እኔ ለእስራኤላውያን ወደምሰጣት ወደ ከነዓን ምድር ሄደው የምድሪቱን ሁኔታ መርምረው እንዲመለሱ ላካቸው፤”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለእስራኤል ልጆች የምሰጣትን የከንዓንን ምድር ይሰልሉ ዘንድ ሰዎችን ላክ፤ ከአባቶች ነገድ ሁሉ እያንዳንዱ በመካከላቸው አለቃ የሆነ አንድ ሰው ትልካላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 13:2
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሙሴም ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ችሎታ ያላ​ቸ​ውን ሰዎች መረጠ፤ በሕ​ዝ​ቡም ላይ የሺህ አለ​ቆች፥ የመቶ አለ​ቆች፥ የአ​ም​ሳም አለ​ቆች፥ የዐ​ሥ​ርም አለ​ቆች አድ​ርጎ ሾማ​ቸው።


እንደ እየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት ከየ​ነ​ገዱ አለ​ቆች አንድ አንድ ሰው ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ ለሕ​ዝቡ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና ጸሐ​ፍት ይሆኑ ዘንድ የም​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን፥ ሰባ ሰዎች ሰብ​ስ​ብ​ልኝ፤ ወደ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን አም​ጣ​ቸው፤ በዚ​ያም ከአ​ንተ ጋር አቁ​ማ​ቸው።


ምድ​ሪ​ቱን ይሰ​ልሉ ዘንድ ሙሴ የላ​ካ​ቸው ሰዎች ስሞች እነ​ዚህ ናቸው። ሙሴም የነ​ዌን ልጅ አው​ሴን ኢያሱ ብሎ ጠራው።


ሙሴም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ከፋ​ራን ምድረ በዳ ላካ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆች ነበሩ።


ምድ​ሪ​ቱን ይሰ​ልሉ ዘንድ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ክ​ኋ​ቸው ጊዜ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ዲህ አድ​ር​ገው አል​ነ​በ​ረ​ምን?


ምድ​ሪ​ቱ​ንም ርስት አድ​ር​ገው የሚ​ያ​ካ​ፍ​ሏ​ቸው ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ አለቃ ይወ​ስ​ዳሉ።


ከእ​ና​ን​ተም ጥበ​በ​ኞ​ችና ዐዋ​ቂ​ዎች፥ አስ​ተ​ዋ​ዮ​ችም የሆ​ኑ​ትን ሰዎች ወሰ​ድሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ አለ​ቆች፥ የሻ​ለ​ቆ​ችም፥ የመቶ አለ​ቆ​ችም፥ የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችም፥ የዐ​ሥር አለ​ቆ​ችም፥ ለፈ​ራ​ጆ​ቻ​ች​ሁም ጻፎች አድ​ርጌ ሰየ​ም​ኋ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ውጡ፤ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁ​ንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ካ​ችሁ ጊዜ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዐመ​ፃ​ችሁ፤ በእ​ር​ሱም አላ​መ​ና​ች​ሁም፤ ቃሉ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።


አሁ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ዐሥራ ሁለት ሰዎ​ችን ምረጡ፤ ከየ​ነ​ገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን።