የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 24:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያ​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴሎ ሰበ​ሰበ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጠራ​ቸው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አቆ​ማ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ኢያሱ የእስራኤልን ነገዶች ሁሉ በሴኬም ሰበሰበ፤ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች፣ መሪዎች፣ ፈራጆችና ሹማምት ጠራ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበሰበ፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች አለቆቻቸውንም ፈራጆቻቸውንም ሹማምንቶቻቸውንም ጠራ። እነርሱም በጌታ ፊት ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢያሱ የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ በሴኬም በአንድነት ሰበሰበ፤ ሽማግሌዎችን፥ አለቆቻቸውን፥ ዳኞችንና የእስራኤልን የጦር አዛዦች ሁሉ ጠራ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ተሰበሰቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴኬም ሰበሰበ፥ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች አለቆቻቸውንም ፈራጆቻቸውንም ሹማምቶቻቸውንም ጠራ። እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 24:1
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብ​ራ​ምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚ​ያች ምድር አለፈ፤ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በዚ​ያን ጊዜ በዚ​ያች ምድር ነበሩ።


በእ​ጃ​ቸው ያሉ​ት​ንም እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክት ሁሉ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም ያሉ​ትን ጉት​ቾች ለያ​ዕ​ቆብ ሰጡት፤ ያዕ​ቆ​ብም በሴ​ቄም አጠ​ገብ ካለ​ችው ዛፍ በታች ቀበ​ራ​ቸው። እስከ ዛሬም ድረስ አጠ​ፋ​ቸው።


እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ያነ​ግ​ሡት ዘንድ ወደ ሰቂማ መጥ​ተው ነበ​ርና ሮብ​ዓም ወደ ሰቂማ ሄደ።


ንጉ​ሡም ላከ፤ የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ ወደ እርሱ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።


ስለ​ዚ​ህም ወዲ​ያ​ውኑ ወደ አንተ ላክሁ፤ ወደ እኛ በመ​ም​ጣ​ት​ህም መል​ካም አደ​ረ​ግህ፤ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ህን ሁሉ ልን​ሰማ እነሆ፥ እኛ ሁላ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚህ አለን።”


የም​ታ​ደ​ር​ጉት ሁሉ ይከ​ና​ወ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ የዚ​ህን ቃል ኪዳን ቃሎች ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።


በን​ፍ​ታ​ሌም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በገ​ሊላ ቃዴ​ስን፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሴኬ​ምን፥ በይ​ሁ​ዳም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ኬብ​ሮን የም​ት​ባ​ለ​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ለዩ።


ኢያሱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሁሉ፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ሹሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጠርቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ እነሆ ሸም​ግ​ያ​ለሁ፤ ዘመ​ኔም አል​ፎ​አል፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወጥ​ተው ወደ ቤቴል መጡ፤ አለ​ቀ​ሱም፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​መጡ፤ በዚ​ያም ቀን እስከ ማታ ድረስ ጾሙ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረቡ።


ዛሬ ግን ከመ​ከ​ራ​ች​ሁና ከጭ​ን​ቃ​ችሁ ሁሉ ያዳ​ና​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንቃ​ችሁ፦ ‘እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን’ አላ​ች​ሁት። አሁ​ንም በየ​ነ​ገ​ዳ​ች​ሁና በየ​ወ​ገ​ና​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁሙ” አላ​ቸው።