የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 22:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኢያ​ሱም መረ​ቃ​ቸው፤ አሰ​ና​በ​ታ​ቸ​ውም፤ ወደ ቤታ​ቸ​ውም ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ኢያሱ መርቆ አሰናበታቸው፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ተመለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱም ባረካቸው፥ እንዲሄዱም አሰናበታቸው፤ ወደ ቤታቸውም ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢያሱም ባርኮ አሰናበታቸውና ወደ ሰፈራቸው ሄዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢያሱም መረቃቸው፥ ሰደዳቸውም፥ ወደ ቤታቸውም ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 22:6
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብ​ራ​ም​ንም ባረ​ከው፤ “አብ​ራም ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ለፈ​ጠረ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረከ ነው፤


ያዕ​ቆ​ብም ፈር​ዖ​ንን ባረ​ከው፤ ከፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ወጣ።


ዮሴ​ፍም ያዕ​ቆ​ብን አባ​ቱን አስ​ገ​ብቶ በፈ​ር​ዖን ፊት አቆ​መው፤ ያዕ​ቆ​ብም ፈር​ዖ​ንን ባረ​ከው።


ዳዊ​ትም የሚ​ቃ​ጠ​ልና የሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት ማሳ​ረ​ግን ከፈ​ጸመ በኋላ ሕዝ​ቡን በሰ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም መረቀ።


ለሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ለወ​ን​ዱም፥ ለሴ​ቱም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አን​ዳ​ንድ እን​ጀራ፥ አን​ዳ​ን​ድም የሥጋ ቍራጭ፥ አን​ዳ​ን​ድም ጽዋዕ ወይን አከ​ፋ​ፈለ። ሕዝ​ቡም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ቤቱ ሄደ።


ዳዊ​ትም ቤተ ሰቡን ሊመ​ርቅ ተመ​ለሰ። የሳ​ኦል ልጅ ሜል​ኮ​ልም ዳዊ​ትን ለመ​ቀ​በል ወጣ​ችና ሰላ​ምታ ሰጠ​ችው፥ “ከሚ​ዘ​ፍ​ኑት አንዱ እን​ደ​ሚ​ገ​ለጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ሚስ​ቶች ፊት በመ​ገ​ለጡ ምንኛ የተ​ከ​በረ ነው!” አለች።


በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕዝ​ቡን አሰ​ና​በተ፤ እነ​ር​ሱም ንጉ​ሡን መረቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለባ​ሪ​ያው ለዳ​ዊ​ትና ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ስላ​ደ​ረ​ገው ቸር​ነት ሁሉ በል​ባ​ቸው ደስ ብሏ​ቸው፥ ሐሴ​ትም አድ​ር​ገው ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው ሄዱ።


እንደ ትእ​ዛ​ዙም ሳይ​ሆን ከኤ​ፍ​ሬ​ምና ከም​ናሴ፥ ከይ​ሳ​ኮ​ርና ከዛ​ብ​ሎ​ንም ወገን እጅግ ሰዎች ሳይ​ነጹ ፋሲ​ካ​ውን በሉ።


ሙሴም ሥራ​ውን ሁሉ አየ፤ እነ​ሆም፥ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አድ​ር​ገ​ውት ነበር፤ ሙሴም ባረ​ካ​ቸው።


ስም​ዖ​ንም ባረ​ካ​ቸው፤ እና​ቱን ማር​ያ​ም​ንም እን​ዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ለብ​ዙ​ዎች ለመ​ው​ደ​ቃ​ቸ​ውና ለመ​ነ​ሣ​ታ​ቸው፥ ለሚ​ቃ​ወ​ሙ​ትም ምል​ክት ይሆን ዘንድ የተ​ሠ​የመ ነው፤


እስከ ቢታ​ን​ያም ወደ ውጭ አወ​ጣ​ቸው፤ እጁ​ንም አን​ሥቶ በላ​ያ​ቸ​ውም ጭኖ ባረ​ካ​ቸው።


ኢያ​ሱም የቄ​ኔዝ ልጅ፥ የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌ​ብን ባረ​ከው፤ ኬብ​ሮ​ን​ንም ርስት አድ​ርጎ ሰጠው።


ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን አሰ​ና​በተ፤ ሁሉም ወደ​የ​ቦ​ታ​ቸው ገቡ።


ሳሙ​ኤ​ልም የን​ጉ​ሡን ሥር​ዐት ነገ​ራ​ቸው፤ በመ​ጽ​ሐ​ፍም ጻፈው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አኖ​ረው። ሳሙ​ኤ​ልም ሕዝ​ቡን ሁሉ ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው አሰ​ና​በ​ታ​ቸው። ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው ሄዱ።


ያን​ጊ​ዜም ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎ​ችን ከእ​ስ​ራ​ኤል መረጠ፤ ሁለ​ቱም ሺህ በማ​ኪ​ማ​ስና በቤ​ቴል ተራራ ከሳ​ኦል ጋር ነበሩ፤ አን​ዱም ሺህ በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ከልጁ ከዮ​ና​ታን ጋር ነበሩ፤ የቀ​ረ​ው​ንም ሕዝብ እያ​ን​ዳ​ን​ዱን ወደ ድን​ኳኑ አሰ​ና​በተ።


ዔሊም ሕል​ቃ​ና​ንና ሚስ​ቱን ባረ​ካ​ቸው፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አገ​ባ​ኸው ስጦታ ፈንታ ከዚ​ህች ሴት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘር ይስ​ጥህ” አለው፤ እነ​ር​ሱም ወደ ቤታ​ቸው ገቡ።