ኢያሱ 15:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር ዳርቻ ወደ ሊባ እስከሚወስደው መንገድ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የደቡብ ወሰናቸው፣ ከጨው ባሕር ደቡባዊ ጫፍ ካለው የባሕር ወሽመጥ ይነሣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ ትይዮ እስከ ባሕሩ ልሳን ድረስ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቡባዊው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ ትይዩ እስከ ሆነው እስከ ልሳነ ምድሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደቡብም በኩል ያለው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ እስከሚያይ እስከ ባሕር ልሳን ነበረ። |
እግዚአብሔርም የግብፅን ባሕር ያደርቃል፤ በኀይለኛም ነፋስ እጁን በወንዙ ላይ ያነሣል፤ ሰባት ፈሳሾችንም ይመታል፤ ሰዎችም በጫማቸው እንዲሻገሩ ያደርጋቸዋል።
የምሥራቁም ድንበር በሐውራን በደማስቆና በገለዓድ በእስራኤልም ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል። ከሰሜኑ ድንበር ጀምሮ እስከ ምሥራቁ ባሕር እስከ ታማር ድረስ የምሥራቁ ድንበር ይህ ነው።
እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “ይህ ውኃ ወደ ምሥራቅ ወደ ገሊላ ይወጣል፤ ወደ ዓረባም ይወርዳል፤ ወደ ባሕሩም ይገባል፤ ወደ ባሕሩም ወደ ረከሰው ውኃ በገባ ጊዜ ውኃውን ይፈውሰዋል።
ከዚያም በአቅረቢን ዐቀበት ፊት ይሄዳል፤ ወደ ጺንም ይወጣል፤ በቃዴስ በርኔ ወደ ደቡብ በኩል ይወጣል፤ በአስሮንም በኩል ያልፋል፤ ወደ ሰራዳም ይወጣል፥ ወደ ቃዴስ ምዕራብም ይዞራል።
ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀርያትያርም አውራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።